ብሔራዊ ባንክ በተለያዩ መተግበሪያዎች የሚደረጉ የዲጂታል ግብይቶችን አገደ

Date:


የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ክሪፕቶ ከረንሲን ጨምሮ ፈቃድ በሌላቸው የተለያዩ መተግበሪያዎች የሚደረጉ የአቻ የዲጂታል ግብይቶችን በጊዜያዊነት አግዷል፡፡

ባንኩ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው÷ በተዘረጉ የቁጥጥር ማዕቀፎች መሰረት በተደረገ ክትትል ግለሰቦች ከባንኩ ፈቃድ በሌላቸው የተለያዩ መተግበሪያዎች ግብይቶችን እየፈፀሙ ነው ብሏል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ የዲጂታል ግብይት ፍላጎት እየጨመረ በመጣበት በዚህ ወቅት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ ገልጾ፤ ግለሰቦች ግብይት በሚፈፅሙበት ወቅት በትክክለኛ መረጃ ላይ ተመስርተው ሊሆን እንደሚገባ አሳስቧል፡፡

በተለይም የዲጂታል ግብይቶች የገበያ ተለዋዋጭነትን፣ የውጭ ምንዛሪ ዋጋ ማሳሳትን፣ የሳይበር ወንጀልን፣ የግብይት ግልፀኝነት ችግሮችን የሚያስከትሉ እንዲሁም የህገ ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የፋይናንስ ሽብርተኝነት ክልከላ ማዕቀፍ የሌላቸው መሆኑን አብራርቷል፡፡

ባንኩ ዲጂታል የግብይት ቴክኖሎጂዎች ደህንነታቸው እንዲጠበቅ የሚያስችል አጠቃላይ የቁጥጥር ማዕቀፍ በመዘርጋት እየሰራ መሆኑን አስገንዝቧል፡፡

በቀጣይም የፋይናንስ መረጋጋትን እና የብሔራዊ የክፍያ ስርዓቱን ታማኝነት ለመጠበቅ ከዓለም አቀፍ የፋይናንስ ተቆጣጣሪዎች እና ከሀገር ውስጥ ባለድርሻ አካላት ጋር ቀጣይነት ያለው ምክክር እንደሚደረግ ጠቁሟል፡፡

የግብይት ቁጥጥር ማዕቀፍ ይፋ እስከሚሆን ድረስ ክሪፕቶ ከረንሲን ጨምሮ ፈቃድ በሌላቸው የተለያዩ መተግበሪያዎች የሚደረጉ የአቻ የዲጂታል ግብይቶች የተከለከሉ መሆኑን ባንኩ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...