ተንኮል አዘል መተግበሪያዎችን (Malware) እንዴት እንከላከል?

Date:


ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች (Malware) ትክክለኛ ሶፍትዌሮችን/መተግበሪያዎችን በመምሰል ሰዎች በቀላሉ እንዲሳቡ/እንዲታለሉ እና ለጥቃት እንዲጋለጡ በማድረግ ያልተፈቀደ ተግባርን የሚፈፅሙ ናቸው።

ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች እንደ ቴሌግራም/ዋትስአፕ ባሉ ማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች ላይ በስፋት እየተሰራጩ የሚገኙ ሲሆን፣ ስማቸውን በመቀያየር እንደ ጤና፣ ግብርና፣ ትምህርት፣ ፋይናንስ እና ባንኪንግ የመሳሰሉ ዘርፎች ላይ አገልግሎት የሚሰጡ መተግበሪያዎችን በመምሰል ጥቃት በማድረስ ላይ ይገኛሉ።

የተንኮል አዘል መተግበሪያዎች (Malware)  ጥቃቶች እና ባህርያት

•  የእጅ ስልኮቻችን ለአካል ጉዳተኞች እና የተለያዩ የጤና እክል ላለባቸው ተጠቃሚዎች አገልግሎት ምቹ እና ቀላል እንዲሆን ለማስቻል ሲባል እንደ በድምፅ ማዘዝ የመሳሰሉ የተደራሽነት አገልግሎቶችን እንደ ክፍተት በመጠቀም ጥቃቶችን ይሰነዝራሉ፣

•  ተንኮል አዘል መተግበሪያዎች የእጅ ስልኮቻችንን ስክሪን ማየት፣ ኢሜይል/አጭር የፅሁፍ መልዕክት ማንበብ፣ ትክክለኛ የሚመስሉ ሀሰተኛ የመግቢያ ገፆችን በማሳየት የምናስገባቸውን ሚስጥራዊነት ያላቸውን የይለፍ-ቃሎች በቀላሉ በመመንተፍ ጥቃቶችን ይሰነዝራሉ፣

•  የፋይናንሻል ግብይቶችን ከተጠቂው እውቅና ውጪ ይፈፅማሉ፣

•  ተጠቂው የሚጠቀምባቸው ማህበራዊ ትስስር ድረ-ገፆች ላይ በመግባት ለሁሉም ጓደኞች መተግበሪያውን ያዛምታሉ፣

•  የአንድ ተጠቃሚን ትክክለኛነት ለማረጋገጥ የሚላከውን የአንድ ጊዜ ይለፍ-ቃል (OTP) በመመንተፍ ባለ ሁሉት ደረጃ ማረጋገጫን (Two Factor Authentication) ያልፋሉ፣

•  የእጅ ስልካችንን በመቆለፍ ገንዘብ ይጠይቃሉ፣

•  በድብቅ እኛን በመሰለል ለሌላ ቀጣይ ጥቃት ያመቻቻሉ።

መከላከያ መንገዶች

•  ካልታመኑ ምንጮች መተግበሪያዎችን ከማውረድ ይቆጠቡ፣
•  እንደ ፕሌይ ስቶር፣ አፕ ስቶር፣ አማዞን አፕ ስቶር ወይም ሳምሰንግ ጋላክሲ ስቶር ጥብቅ የደህንነት ፍተሻዎችን የሚያደርጉ ይፋዊ የመተግበሪያ ማከማቻዎችን ብቻ ይጠቀሙ፣
•  ከአጠራጣሪ ኢ-ሜይሎች የሚላክሎትን ማስፈንጠሪያም (suspicious links) ሆነ ፋይል (Attachment) ሳያረጋግጡ ከመክፈት ይቆጠቡ፣
•  መተግበሪያዎች የካሜራ፣ የማይክራፎን፣ የጥሪ መዝገብ፣ የቦታ እና የፋይል የመሳሰሉ ፍቃዶችን (Permission) ሲጠይቁ አስፈላጊነቱን የራስዎን ጥናት በማድረግ ፍቃዱን ይገድቡ፣
•  የባንክ መግለጫዎችዎን እና የግብይት ታሪክዎን በመደበኛነት ይከታተሉ፣
•  ማንኛውንም አጠራጣሪ ወይም ያልተፈቀዱ ግብይቶች ሲያስተውሉ ወዲያውኑ 951 በመደወል ያሳውቁ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ በመካከለኛው ምስራቅ ለሚገኙ ዜጎቿ አስቸኳይ ማስጠንቀቂያ አስተላለፈች

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በኢራን ላይ አዳዲስ ወታደራዊ ጥቃቶች ሊሰነዘሩ...

ፍትህ ተሰውቶ የጉልበት ብልጫ የገነነበት ውሳኔ ነው

ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የክፍያ ስርዓት መመሪያ (Financial...

“ተፅዕኖ ፈጣሪዎች” የተባሉ ግለሰቦች በምክክሩ እንዲሳተፉ በምን መስፈረት ተመረጡ?

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 17ኛ ቀን ውሎ የክልል ተወካዮች ጉባኤ...

የአሜሪካ ጦር እስራኤልን ከኢራን መከላከሌን ላቆም እችላለሁ አለ

በመካከለኛው ምስራቅ ያለው ውጥረት በከፍተኛ ሁኔታ በናረበት በዚህ...