የማገገሚያ ተቋሙ በጦርነቱ ለተጎዱ ሴቶች፣ ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸውና የስነልቦና ቀውስ ለገጠማቸው ሴቶች አገልግሎት የሚሰጥ ነዉ ተብሏል፡፡
የቱርክ የእርዳታ ድርጅት ኤጀንሲ ቲካ ፤ ሱዳናውያኑን ለማገዝ በፖርት ሱዳን ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ማዕከል ከፍቻለሁ ብሏል፡፡
ተቋሙ የተከፈተው በተለይም በጦርነቱ ምክንያት ከካርቱም ገዚራና ሴናር ከተባሉ ከተሞች የተፈናቀሉ ሴቶች የሚያርፉበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ሴቶቹ በጦርነቱ ምክንያት የተለያዩ ችግሮች የገጠማቸው እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከነዚህ ችግሮችም እንዲወጡ የተለያዩ ስልጠናዎችና ትምህርቶች እንዲሁም ድጋፎች እንደሚሰጣቸዉ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡
ሶስት አመት በሞላው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሚሊዮኖች ሲፈናቀሉ 20ሺህ የሚጠጉ ሱዳናውያን ህይወታቸውን ማጣታቸዉን የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡
