ታላቁ የሕዳሴ ግድብ የራሱ የሆነ የቱሪዝም ብራንድ እንዲኖረው ጥናት እየተደረገ ነው

Date:

በግድቡ ሥፍራ የሚገኘው የጥናት ቡድን የጥናቱን ውጤት በቅርቡ ይፋ እንደሚያደረግ ተገለጿል፡፡

የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ እንደገና አበበ ለሀገር ውስጥ ጋዜጣ እንደገለጹት፤ የቱሪዝም ሚኒስቴር “የዓባይ ግድብ ምን ዓይነት የቱሪዝም ተዝናኖትን ሊፈጥር ይችላል?”

በሚል ውሃው እና መልክዓ ምድሩ በቅንጅት በሚፈጥሩት የቱሪዝም መስኅብ የራሱ የሆነ የቱሪዝም ብራንድ እንዲኖረው እየተሠራ ነው፡፡

ግድቡ ከሚሰጠው ከፍተኛ የዓሣ ምርት ባሻገር ያሉት የቱሪዝም ዕድሎች፦

ግድቡ የሚያርፍበት ቦታ የውሃውን ይዞታ ጨምሮ 1 ሺህ 740 ስኩዌር ኪሎ ሜትር መሸፈኑ፣

ግድቡ የሚይዘው 74 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ ውሃ ወደ ኋላ 246 ኪሎ ሜትር መርዘሙ፣

እያንዳንዳቸው ከአምስት ሔክታር በላይ ስፋት ያላቸው 70 ደሴቶች መፈጠራቸው፣

2 ሺህ 800 ሔክታር ስፋት የሚኖረው አንድ ትልቅ ደሴት፡፡

ግድቡን ወደ ዋነኛ የቱሪስት መስኅብነት ለመቀየርም በትኩረት እየተሠራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው፤ የዓባይ ግድብ የቱሪዝም ዘርፉን የሚያነቃቃ ልዩ ስጦታ መሆኑን ገልጸዋል።

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በቬንዝዌላ በደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ የ32 ሰዎች ህይወት አልፏል

በቬንዙዌላ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የታወጀ ሲሆን 7.2 እና 7.5...

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ “ሉሲ” ላገኟት ፕሮፌሰር የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው ሴኔት ሰኔ 16 ቀን 2018 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ፥...

የሳህለወርቅ ዘውዴ አዲሱ አለም አቀፍ ሹመት በተመድ ልዩ ተልእኮ ተሰጣቸው

የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዝደንት ወይዘሮ ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ ዋና ፀሀፊ...

በሳዑዲ በምሕረት የተለቀቁ 320 ኢትዮጵያውያን

በሳዑዲ አረቢያ የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምህረት አዋጅ ከተሰጣቸው 1...