ትራምፕ እና ፑቲን ከጀርባ በሚስጥር እየተስማሙብን ነዉ

Date:



‎ዩክሬን ዋናዋ ባለጉዳይ እያለሁ አሜሪካና ሩሲያ እኔን ሳያማክሩ በጓሮ በኩል እየተስማሙ እየተደራደሩ እየተወያዩ እንደሚገኝና ጉዳዩም እንዳሳሰበኝ አለም ይወቅልኝ ማለቷ ተሰማ ።

‎የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ የዩኤስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር ከመደወል በፊት እኔን ማናገር ነበረባቸው ይህን ሳያደርጉ ከፑቲን ጋር መወያየታቸው “በጣም አስደሳች አይደለም” ሲሉ መናገራቸው ተነግሯል ።

‎ዘለንስኪ ይህንን ያሉት ትራምፕ ከፑቲን ጋር “ረዥም እና ውጤታማ የስልክ ጥሪ” እንዳደረጉ በመግለጽ ሁለቱ በዩክሬን ጦርነት ላይ የተኩስ አቁም ድርድር ለመጀመር ተስማምተዋል ማለታቸው ተከትሎ ሲሆን ዘሌንስኪ በጀርመን በሙኒክ የፀጥታ ኮንፈረንስ ላይ ባደረጉት ንግግር የ አውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ዲፕሎማቶችን ዩክሬንን ወደ ጎን በመተው እና አውሮፓን ሳያማክሩ ከሩሲያው ቭላድሚር ፑቲን ጋር በመገናኘታቸው ዋይት ሀውስን ነቅፈዋል።
‎።

‎የሁለቱ መሪዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ዩክሬን የጠፋችውን ግዛቷን ሙሉ በሙሉ ለማስመለስ ወይም የኔቶ አባልነት ባልተረጋገጠበት ሁኔታ ትራምፕ ለፑቲን ልባቸውን እየሰጡ ተደርጎ በመወሰዱ ኪየቭ ስለ ራሷ ጉዳይ በሚደረጉ ውይይቶች ወደ ጎን ተትታለች የሚል ስጋት ፈጥሯል።

‎ይህን ተከትሎ አስተያየት የሰጡት ዘሌኒስኪ” ዩክሬን ለዋሽንግተን ቅድሚያ እንደምትሰጥ እያታወቀ‎”የዩክሬን-አሜሪካ ስብሰባዎች ለኛ ቅድሚያ ይሰጡናል” ብለን እያሰብን ባለንበት ወቅት ከጀርባ የሚደረጉ ዉይይቶች አስፈላጊ አለመሆናቸውን ገልፀዋል ።

‎”ከእንደዚህ አይነት እኛን ያላሳተፈ ስብሰባዎች በጓዳ በኩል ማድረግ ፑቲንን ክብር መስጠት ነዉ ” ያሉ ሲሆን አክለዉም ከፑቲን ጋር መወያየትም ካስፈለገ ጦርነቱን እንዴት እንደሚቆም እቅድ ከተሰራ በኋላ መሆን ነበረበት በጋር ስንስማማ ብቻ ከሩሲያውያን ጋር መነጋገር ተገቢ ነው ብዬ አስባለሁ.” ሲሉ ተናግረዋል ።

‎የዩናይትድ ስቴትስ መሪን በመያዝ ከደህንነት ዋስትና ውጭ በማድረግ ሩሲያ እንደገና በዩክሬን ላይ ጥቃት ልትሰነዝር እንደምትችል አስጠንቅቀዋል ሲል የዘገበው ሞስኮ ታይምስ ነዉ ።


‎የኔታ ቲዩብ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

መረጃ በማይሰጡ ኃላፊዎች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ የሚያስችል ሕግ ተዘጋጀ

የመገናኛ ብዙሃን እና የመረጃ ነፃነት የየራሳቸው ባህሪ ቢኖራቸውም እስካሁን...

የ30 ዓመታትን ጉዞ የሚዘክረው ዳሸን ኤክስፖ

የዳሸን ባንክን 30ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው...

‹‹ሀገር ጥለው የጠፉና ድርጅቶቻቸውን ለመዝጋት የተገደዱ አሉ››

አቶ አለማየሁ ከተማ(የኢትዮጵያ ሪልስቴት አልሚዎች ማኅበር ፕሬዝዳንት) ግዮን መጽሔት :-...

የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ

የሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ...