የሰላም ስምምነት ሳይፈጸም የንግድ መርከቦች ጉዞ እንደማይጀምሩ የነዳጅ ጫኝ ኩባንያ ኃላፊ ተናገሩ

Date:

የሲውዲን ነዳጅ አጓጓዥ ኩባንያ የሆነው ‘ስቴና በልክ’ ዋና ስራ አስፈጻሚ በአሁኑ ሰዓት የኩባንያው መርከቦች በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል የሚያልፉበት “ምንም ዕድል” እንደሌለ ተናገሩ።

የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኤሪክ ሃኔል ከቢቢሲ ሬዲዮ 4 ‘ቱዴይ’ ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ “ይህንን አይነት እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት” በውሃ መስመሩ በኩል በሰላም ለማለፍ “ከሁለቱም፤ ከኢራን እና አሜሪካ የደኅንነት ዋስትና ያስፈልገናል” ብለዋል።

የንግድ መርከቦች በድጋሚ ጉዞ እንዲጀምሩ የሚያስችለው አስፈላጊ ሁኔታ ሊፈጠር የሚችለው የሰላም ስምምነት ሲፈረም ብቻ መሆኑን ገልጸዋል።

“ከጥቂት ሳምንታት በፊት፣ እስከ ባለፈው ሳምንት ድረስ ባለው ጊዜ በአንድ ሳምንት ገደማ ውስጥ እንድናልፍ የሚያደርግ አንድ ነገር ይፈጠራል የሚል ተስፋ ነበረን” ያሉት ዋና ሥራ አስፈጻሚው፤ አሁን ግን ሁኔታው “የተቆለፈ” ሆኗል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በ2026 የዓለም ዋንጫ ላይ ለተለያዩ ብሔራዊ ቡድኖች የሚጫወቱ ወንድማማቾች

የ2026 የፊፋ የዓለም ዋንጫ ከመላው ዓለም የተውጣጡ ምርጥ ተጫዋቾችን...

ኢንፊኒቲ ለቤትና ለመኪና መግዣ ብድር እየሰጠ እንደሚገኝ አስታወቀ

ኢንፊኒቲ ኃላፊነቱ የተወሠነ መሠረታዊ የቁጠባ እና ብድር ኀብረት ሥራ...

የአዲሱ የወንጀል ህግ ስነ-ስርዓት የእርማት ስራዎች ሳይጠናቀቁ በሥራ ላይ እየዋለ ነው

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ላለፉት 64 ዓመታት...

ናይጄሪያው ዩናይትድ ካፒታል በኢትዮጵያ የመጀመሪያውን የውጭ ኢንቨስትመንት ባንክ ፈቃድ አገኘ

​የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለሥልጣን በሀገሪቱ የካፒታል ገበያ ታሪክ ለመጀመሪያ...