ቻይንኛ ቋንቋን በ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለመስጠት ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ ነዉ

Date:

ከቻይና መንግስት ጋር ባለው ግንኙነት መሰረት መስከረም ላይ በሚጀምረው የ2019 ትምህርት ዘመን በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የቻይንኛ ቋንቋ እንዲሰጥ ለማድረግ ዝግጅቶች እየተጠናቀቁ እንደሚገኝ የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በእነዚህ ትምህርትቤቶች ውስጥ ቻይንኛን የሚያስተምሩ መምህራንን ለማስመጣትም ርብርብ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጿል።

በትምህርት ሚኒስቴር አጠቃላይ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ፕሮግራሞችና ጥራት ማሻሻል መሪ አስራአስፈፃሚ ዶ/ር ዮሀንስ ወጋሶ የአዳሪ ትምህርትቤት ተማሪዎች የተሻለ ውጤት ያላቸውና በመለያ ፈተና አልፈው የሚገቡ መሆናቸውን አንስተዋል።

እነዚህ ተማሪዎች በአለምአቀፍ ደረጃ ውጤታማና ስኬታማ እንዲሆኑ ለማድረግም የተለያዩ የውጪ ሀገር ቋንቋዎችን እንዲማሩ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በተለይም ደግሞ ተማሪዎች የከፍተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በውጪ ሀገር የመከታተል እድል ያላቸው በመሆኑ ለዛ እንዲጠቅማቸው የቋንቋ ትምህርቱ እንደሚሰጥ አመላክተዋል።

እንዲማሩ ከሚደረጉት ቋንቋዎች መካከል ደግሞ በቀጣዩ የ2019 የትምህርት ዘመን የቻይንኛ ቋንቋን እንዲማሩ ለማስቻል የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

ከቻይንኛ በተጨማሪም ሌሎች አለምአቀፍ ቋንቋዎችን በማጠናከር የማስተማር ስራው እንደሚቀጥል ዶ/ር ዮሀንስ አስታውቀዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢትዮጵያ እና የቻይና አየር መንገዶች የጋራ ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እና ቻይና ሳውዘርን አየር መንገድ በቻይና...

ሁቲዎች በሳዑዲ የነዳጅ ኩባንያ አስተዳደር ሕንጻ ላይ በፈጸሙት ጥቃት በእሳት ተያያዘ

የሳዑዲ አረቢያ የኢነርጂ ሚኒስቴር በአገሪቱ ምሥራቃዊ ግዛት የሚገኘው ከዓለም...

የሹመት ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)  ሹመት የሰጧቸው አመራሮች፡- 1. አቶ...

እንደዚህ ዓይነቱ ብልሹ ኣሰራርን ካላረምን በቀር መልካም ኣስተዳደርን …

በኣጠቃላይ በዚህ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኣጠቃላይ...