በአገር ውስጥ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ ፈጣን ዕድገት እያሳየ የሚገኘው አሃዱ ባንክ፣ በላቀ ደረጃ ለመስፋፋትና የገበያ ድርሻውን ለማሳደግ የሚረዳውን ባለ 15 ፎቅ በከፊል የተገነባ ሕንፃ በሜክሲኮ አካባቢ በባለቤትነት መያዙ ታወቀ።
ካፒታል ከምንጮቿ ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ባንኩ የገዛው ይህ ሕንፃ ሁለት የምድር ውስጥ ወለሎችና 15 የተደራረቡ ፎቆች ያሉት ነው።
አሃዱ ባንክ ሕንፃውን በባለቤትነት ሊይዝ የቻለው ንብ ኢንተርናሽናል ባንክ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ጨረታ ላይ ከፍተኛውን ዋጋ አቅርቦ በማሸነፉ እንደሆነና ጨረታውም በይፋ ተቀባይነት ማግኘቱን ምንጮች አረጋግጠል።
