አሐዱ ባንክ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሕጋዊ ሰውነት ያገኘበትንና ፤ የባንኩን የምስረታ ጉባኤ ያከናወነበትን እለት ምክንያት በማድረግ ፤ በሰሊሆም የአዕምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል የምሳ ማብላት መርሀ-ግብር አከናውኗል።
ባንኩ ከብሔራዊ ባንክ የሕጋዊ ሰውነት እውቅና ያገኘበትንና ፤ የባንኩን የምስረታ ጉባኤ ያከናወነበትን ቀን ምክንያት በማድረግ ፤ በየዓመቱ የተለያዩ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን የሚወጣበት ስራዎችን እንደሚሰራ የአሐዱ ባንክ የማርኬቲንግ እና የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አብይ ተናግረዋል።
በዚህም ዘንድሮ የታህሳስ 24 ቀን የምስረታ በአሉን በማስመልከት ፤ ለተለያዩ የበጎ አድራጎት ተቋማት የገንዘብና የአይነት ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የተናገሩት ዳይሬክተሩ ፤ ከእነዚህም ውስጥ አንዱ በሆነው በሰሊሆም የአእምሮ ህሙማን መርጃ ማዕከል በመገኘት ፤ በማዕከሉ ለሚገኙ የአዕምሮ ህሙማን ለሁለት ቀን የሚቆይ የምሳ ማብላት መርሀ-ግብር ማስጀመሩን አስታውቀዋል።
አሐዱ ባንክ ማኅበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት በኩል የበጎ አድራጎት ስራውን አሁንም አጠናክሮ እንዲቀጥል የገለፁት ዳይሬክተሩ ፤ በዚህ ሳምንት ከሚደረጉት ስራዎች መካከልም በመቄዶንያ የአዕምሮ ህሙማንና የአረጋውያን መርጃ ማዕከል ተመሳሳይ መርሀግብር እንደሚያካሂድ ተገልፀዋል።
