ዋሽንግተን በቶማሃውክ ሚሳኤል ጭምር እስከ ቴህራን አቅራቢያ ጥቃት ማድረሷን በፕሬዚዳንቷ በኩል ገልፃለች።
ኢራንም በምላሹ በመካከለኛው ምስራቅ የሚገኙ የአሜሪካን ይዞታዎች መታለች።
የ ኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይል “አሜሪካ ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ አፀፋዊ ምላሽ ሰጥቻለሁ ፤በሆርሙዝ ሰርጥ ሁለት መርከቦችን መትቻለሁ” ብሏል።
የአሜሪካው ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንትኮም) ራስን የመከላከል ጥቃቱን መጀመሩን ከማሳወቁም በሻገር ኢራን ተከታታይነት ያለው ትንኮሳ እያደረገችብን እስከሆነ ድረስ እርምጃ እንወሰዳለን ብሏል።
በገሽም፣ባንዳር አባስ እናሲሪክ አካባቢዎች ከፍተኛ ፍንዳታዎች እንደነበሩም የኢራን ሚዲያዊች ዘግበዋል።
በሆርሙዝ ሰርጥ የሚያልፍ የትኛውም ዓይነት መርከብ አይኖርም ያለችው ኢራን ሰርጡ ሙሉ በሙሉ ተዘግቷል በሚልም በሚዲያዎቿ በኩል መረጃ እያወጣች ነው።
የአሜሪካ የቀጠናው ዕዝ ግን የንግድ መርከቦች አሁንም በሆርሙዝ እያለፉ ነው ሲል መግለጫ ሰጥቷል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ 49 ቶማሃውክ ሚሳዔሎችን አሜሪካ እንደተጠቀመችም አሳውቀዋል።
የተወሰኑት ሚሳዔሎች እስከ ቴህራን 40 ኪሎ ሜትር ቀርበው ጥቃት ማድረሳቸውንም እወቁልን ብለዋል።
“የአሜሪካ ጀቶች በኢራን የአየር ክልል ሲንቀሳቀሱ ነበር፤የራዳር ስርዓቶችን፣የየአየር መከላከያ ስርዓቶችን እና፣ወታደራዊ መግባቢያዎችን ዒላማ አድርገናል “ብለዋል።
በሌላ በኩል ትራምፕ የ ኢራን ፖለቲከኞች ጥቃቱ ይቁም ብለው ደውለውልኛል ብለዋል።
ትራምፕ ይህን ቢሉም ኢራን ፈፅሞ አላደረኩትም በሚል ውድቅ አድርጋዋለች።
አይ አር ጂ ሲ እንዳስታወቀው የኤሮስፔስ እና ባህር ኃይሉ ሁለት ዙር ተጨማሪ የጥቃት ማዕበል በአሜሪካ የመካከለኛው ምስራቅ ኃይሎች ላይ አድርሷል።
በ18 ዒላማዎች የአሜሪካን ሀይሎች በሚያስተናግዱ የጦር ሰፈሮች ጥቃት ኢራን ማድረሷም ተወስቷል።
አሜሪካ የዛሬውን ዘመቻ ማጠናቀቋንም አሳውቃለች።
የአልጀዚራና ቢቢሲ
