አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

Date:



በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ የተጣለው የባህር ላይ እገዳ፣ ኢራን በሦስት ሳምንታት ውስጥ ብቻ 4.8 ቢሊዮን ዶላር የነዳጅ ገቢ እንድታጣ አድርጓታል።

የፔንታጎን ባለስልጣናትን የጠቀሰው የአክሲዮስ ዘገባ እንደሚያመለክተው፣ ካለፈው ሚያዝያ 5  ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ በሆነው በዚህ እገዳ ምክንያት 53 ሚሊዮን በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ የጫኑ 31 ታንከሮች በባህር ላይ ቆመው እንዲቀሩ ተደርገዋል።

እገዳው አሜሪካ በተኩስ አቁም ድርድሮች ላይ እንደ መደራደሪያ ለመጠቀም ባሰበችው ስትራቴጂ የተጣለ ሲሆን፣ እስካሁን ከ40 በላይ መርከቦች መንገዳቸውን እንዲቀይሩ ተገደዋል።

በየብስ ላይ ያሉት የነዳጅ ማከማቻዎች አቅማቸው በመሙላቱ ኢራን ያረጁ መርከቦችን እንደ ተንሳፋፊ ማከማቻ ለመጠቀም ብትገደድም፣ በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የማከማቻ ቦታው ሙሉ በሙሉ ካለቀ የነዳጅ ጉድጓዶቿን ለመዝጋት ልትገደድ እንደምትችል ተነግሯል።

አንዳንድ የኢራን መርከቦች የአሜሪካን ክትትል ለማምለጥ በፓኪስታንና ህንድ በኩል ረጅም እና ውድ መንገዶችን በመጠቀም ነዳጁን ለቻይና ለማድረስ እየሞከሩ ሲሆን፣ ፔንታጎን በበኩሉ እርምጃው ኢራን ሽብርተኝነትን ለመደገፍ የምትጠቀምበትን የገቢ ምንጭ ለመምታት የታለመና ውጤታማ ነው ብሎታል።

ይህ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው የንግድ መስመሮችን እንደ ጦር መሳሪያ የመጠቀም እንቅስቃሴ፣ ቀጠናውን ወደ “ቀዝቃዛ ጦርነት” ምዕራፍ እያሸጋገረው መሆኑን ተንታኞች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ

የእግዚአብሔር ሕዝብ ጉባኤ፣ የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አካልና የመንፈስ...

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል

በመቅደላ ጦርነት ጊዜ የተዘረፉ የአጼ ቴዎድሮስ የፀጉር ቁንዳል እና...