የአሜሪካ ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንት ኮም) ኢራን በሆርሙዝ ሰርጥ የአራት ሰው አልባ አውሮፕላን (ድሮን ) ጥቃት ማድረሷን ተከትሎ አፀፋዊ ምላሽ በሆርሙዝ ሰርጥ እና በወሳኝ አካባቢዎች መስጠቱን አሳውቋል።
ፎክስ ኒውስ እንዳስነበበው ዋሽንግተን ስድስት የጦር አውሮፕላኖችን በመጠቀም አራት ዒላማዎችን መትቻለሁ ብላለች።
በሆርሙዝ ዳርቻ ባሉ አካባቢዎች እና በገሽም ደሴት ላይ ጥቃት ደርሷል።
የኢራን ሚዲያዊች በሲሪክ አካባቢም ከፍተኛ ፍንዳታ መሰማቱን እየዘገቡ ይገኛል።
የራዳር እና ሚሳዔል ስርዓቶች ዒላማ መሆናቸውም ተሰምቷል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ሚዲያቸው ላይ ኢራን በንግድ መርከብ ላይ ያደረሰችው ጥቃት ምላሽ ሊሰጠው እንደሚችል ቀደም ሲል ይፋ ማድረጋቸው የሚታወስ ነው።
“ኢራን የሰላም ስምምነት ፈርማለች፤እሱን እናከብራለን” ያሉት ምክትል ፕሬዚዳንት ጄዲ ቫንስ “ጥቃትን በጥቃት እንመልሳለን” ብለዋል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኃይል (IRGC) የአሜሪካን ጥቃት አውግዞ ሁል ጊዜም ቢሆን ዋሽንግተን ቃሏን ታጥፋለች በሚል ከሷል።
የኢራን አብዮታዊ ዘብ የአሜሪካን ዒላማዎች በመካከለኛው ምስራቅ መምታቱንም አሳውቋል።
ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ የደረሰው ጉዳትም ሆነ ፤ኢራን ስለሰጠችው ምላሽ ዝርዝር መረጃ አልተጋራም።
