‹‹አብርሆት›› ያስፈለገን ለምን ነበር?

Date:

የሰው ልጅ አዕምሮ በእውቀት እየላቀ በሄደ ቁጥር እውቀቱ ወደ ሳይንስ ብሎም ከጊዜ ጊዜ ወደ ተሻለ የእውቀት ደረጃ እየተመመ ይሄዳል፡፡ እሱም እንደ መታደል ይሆንና ሀገራት ከሀገራት እየተለዩ አንዱ ከሌላኛው ደምቀው እንዲታዩ ከሚያደርጋቸው ቁልፍ ነገር የዚሁ የእውቀት ጥርቅም የሆነው የእውቀት ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ታዲያ ከእውቀት ከልህቀትም አንፃር የሀገራችን ኢትዮጵያ የአስተውሎት እውቀት ከዘመን ዘመን ከጊዜ ጊዜ እጅጉን እየተዳከመ መጥቷል፡፡ ይህም ለበርካታ የሽግግር ወቅቶች የማሻሻያ ለውጦች ቢደረጉም ከፖለቲካ መቀመሪያነት የዘለለ ጥቅም እና ማኅበራዊ ከበሬታን ብሎም ለውጦችን ይዞ መምጣት የሕልም እንጀራ ከሆነበት ዘመናት እንደ ወላድ አምጠው እየማቀቁ ወልደውታል፡፡

በርግጥ የእውቀቱ ምሕዳር እንመራዋለን የሚሉ አካላት በሙሉ ማለት በሚቻልበት መጠን ከፖለቲካ እና ከወገንተኝነት እንደ መዥገር የተጣበቀ የበሽታ መዘውር ያለበት ነገር ግን በሁሉም የትምህርት ዘርፍ የተመረቀ ቢሆንም ሥራው እና ተግባሩ እውነቱም ሀቁም በስሪንጅ የተወጋ ይመስል ከፖለቲካ ጉያ ሳይለይ ሥራውን በአግባቡ እና ሙያው የሚጠይቀውን ሥርዓት ተከትሎ የመሥራት ሂደቱ እጅጉን ጥያቄ ውስጥ የገባ ጉዳይ ነው፡፡

በትምህርት ዙሪያም በዐሥራ አንደኛው ሰዓት የሚደረገው የማስመሰል ወከባ ትውልድን ቢያቆረቁዝ እንጂ በርግጥም ሀገራዊ ፋይዳም ሆነ ጥቅም አይኖረውም፡፡ ታዲያ በዚህ የቀጠለው የማታለል ሥራ ከትውልድ ትውልድ እየተሻገረ መቀጠሉ ወላፈን እያቀጣጠለ የማያባራ የእሳት ዶፍ ሊያዘንብ ይችላል፡፡

ዋናው ቁም ነገር በትምህርት ለሚገኝ እውቀት ወሳኝ የሆነ ትውልድን ለማፍራት የተሟላ እና የተደራጀ የት/ቤት ተቋም የመጀመሪያውን የተሳለጠ ውጤት ለማስገኘት የሚያስችል መንገድ ሲኾን ሌላኛው እና አንገብጋቢው መሠረት በዕውቀት የታነፀ መምህር ብሎም ‹‹ወልዶ ለእድል›› በሚል ፈሊጣዊ ንግግር ሳይሆን ምጣኔ ውስጥ ጥበብ ባለው የቤተሰብ ውስጥ ከፍተኛ ክትትል ጉምቱዎቹ የዕውቀት መገብያ የማዕዘን ድንጋይ ሲሆኑ ታላቁን ድርሻ የሚወስደው የት/ቤት ግብዓቶች ናቸው፡፡

ታዲያ ከነዚህ ፋሲሊቲዎች መካከል የሚጠቀሰው የሥነ ትምህርት ቁሳዊ ግብዓቶች እና ሌሎችም እንዳሉ ሆነው በዋናነት የሚነሳው የቤተ መጻሕፍት /ላይብረሪ/ ታላቁን የዕውቀት መገብያ ግብዓትነቱን በጉምቱነት ይወስዳል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ በሀገራችን የላይብረሪ ተጠቃሚ ብሎም የሚያስጠቅሙ ተቋማቶች መኖር ብሎም ያሉት ውስን ቦታዎች አግባባዊ የሆነ ግልጋሎት አለመስጠታቸው ወንዝ ዳር ተኝቶ ውሃ እንደሚጠማው ፍጡር መቸገር ነው፡፡ ባሉት ተጠቅሞ ተጠቃሚ የሆኑትን ሕብረተሰብ አለማዳረስ ሳያውቁትም ጥምንም ቢሆን ከመጠጡ ላይ እንደማቋረጥ ለአዕምሮ ከሚጠጣ የጥም መቁረጫ ውኃም በላይ መጥፎ እና ዘላለም የማይረኩት ጥማት ነው፡፡

በሀገራችንም ይህ መጥፎ ጥማት መቁረጫውን ከዘመን ዘመን ያሻሻለ ለመምሰል በርካታ የሚዲያ አድማሶችን ቢሰራም የትግበራ ሥራው ግን ‹‹ፍየል ወዲህ ቅዝምዝምም ወዲያ›› የመኾኑ ነገር ለትውልድ አሳሳቢ ችግር ሆኖ ከይሻል ትብስ ሆኖበት ቀጥሏል፡፡

አብርሆት ትልቅ ቤተ መጻሕፍት ተደርጎ እንደ ሀገር በርካታ ዜና እና ጀብዱ ሲሠራበት የከረመ ቢሆንም ይህ ታዲያ እንደሚወራለት እና እንደሚነገርለት እምብዛም ባይሆን ብሎም ሁሉንም እውነት ነው ብሎ ማሰብ እጅጉን ላየው ለማመን የሚከብድ ነው፡፡

በርካታ አብርሆቶችን ዘግቶ በወና ቤት ፎቶ እየተነሱ መለጠፍ በዚህ ዘመን እና ጊዜ ብቻ የሚታይ ክስተት አይደለም፡፡ ነገር ግን ከሌላው ይህን ለየት የሚያደርገው ያሉትን ዘግቶ ሌላ ተዓምር ለመፍጠር ይመስል የሚሰሩ የኋለኛው ቤት ዓይነት እንቆቅልሾች ናቸው፡፡ ታዲያ ሁሌም አሉ ምን ያመጣሉ ብቻ በርካታ ነገሮች ቢጎርፉም ይህ የዐደባባይ ላይ ነገር ቆማሪ ቢያስብል እንጂ ውጤት የለውም እና መንግሥት ከሚመለከተው አካላት ጋር የሚሠሩበት የቀድሞ የተሻለ ብሎም የተሻሉ የሀገራት ተሞክሮን ጥናት በማድረግ የተሻለ ሥርዓት ቢዘረጋ የተሻለ ውጤት ማምጣት የሚቻልበት አቅጣጫ ነው፡፡

ዘመኑ ቴክኖሎጂ ከሀገር ሀገር የሚገናኝበት ራስንም ከሌላው የሚተዋወቁበት እንደመሆኑ መጠን እንደ ኢትዮጵያ በተራድኦ የመጡ የኮምፒውተር ሥሪቶችንም የኢንተርኔት ማለትም የቀደመ ሥራቸውን በተሳለጠ ሁኔታ የሚጀምሩበት ሁኔታ ቢፈጠር ትውልዱንም ከማዘመን ባሻገር ከተፈጥሮ የተሰጠውን ተፈጥሮ ለማዳበር በርካታ የእውቀት አውታሮችን እንዲያካብት የሚያደርጉት ከተፈጥሮ በተጓዳኝ ሁኔታ የበይነ-መረብ አገልግሎት መሆኑ ታስቦበት ወደ ቀደመ ሥራው ቢቻል በተሻለ መልኩ በማዘመን ማስጀመር መልካም ነው፡፡

ይህም ሲባል የትኞቹን እንዳይሆን ነገሩ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ አግራሞትን በሚፈጥር መልኩ 24 ሰዓት ሙሉ አገልግሎት በመስጠት የሚታወቀው የወመዘክር ቤተ መጻሕፍት አገልግሎት ሰዓቱን በሚያስደነግጥ ሁኔታ በአንዴ ወደ 9 ሰዓት የተመለሰበት ሥርዓት ግልፅ ባይሆንም የበርካታ ተጠቃሚዎችን እና የእውቀት ፈላጊዎችን ጥማት እና ስሜት የጎዳ ክስተት እስከዛሬ ድረስ ‹‹ሞኝ አይሙት እንዲህ ያጫውታል›› እንዲሉ ነገሩን ቁዘማ ከሆነ ይኸው ወራቶችም ዘለው ዓመታት እያስቆጠረ ይገኛል፡፡

በርግጥ የተንሸዋረረ አመለካከት ኖሮ ለምን አብርሆት ተገነባ አይደለም፡፡ አብርሆት እንኳን ተገነባ፣ ሺሕ አብርሆቶችንም ለወደፊት አብዝተን እንሻለን፡፡ ታዲያ ግን የነበሩትን አብርሆቶች ዘግቶ በብልጭልጭ ምስል ብቻ ያብረቀረቀውን የመስታወት ግርግዳ እያሳዩ ቀን ለማስቆጠር ይመስል የሚደረግ የእሽቅድምድም መጨረሻው ቢያሳድጉት ልክ በዘንዶ አፍ ውስጥ እንዳለች ምስኪን እንሰሳ መበላትን ቢያተርፍ እንጂ አስወድዶ በትውልድ ልብ ውስጥ የሚያመጣው ርህራሄ እንደማይኖር ከወዲሁ ሊታሰብበት ይገባል፡፡        

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የዲጂታል ኢትዮጵያን ጉዞ ላይ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር ያለመ ሥልጠና አከናወነ

ኩባንያችን ከመንግሥት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጋር በመተባበር...

የኔታንያሁ ድንገተኛ ማስጠንቀቂያ እና የቢሊዮን ዶላር የጋዝ ሚስጥር!

የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከታሪካዊቷ የግብፅ ምድር የሚሰማው...

ኤርትራ ሠራዊቷን በአስቸኳይ ከግዛቷ እንድታስወጣ እና ለድርድር ዝግጁ እንድትሆን ኢትዮጵያ ጠየቀች

የኤርትራ ሠራዊት ተቆጣጣሯቸዋል ካላቸው የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛቶች እንዲወጣ እና...

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደንበኞች ቁጥሩ ከ5.46 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገለፀ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2018 አ.ም የስድስት ወር የዕቅድ አፈፃፀሙን...