ኢትዮጵያ ኑክሌርን ለሰላማዊ አገልግሎት ለመጠቀም ማቀዷን ማሳወቋ አይዘነጋም።
በዘንድሮ የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርትን በሁለተኛ ዲግሪ መስጠት እንደሚጀምር የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታወቀ።
የኢንስቲትዩቱ የድህረ ምረቃ መርሃ ግብር ዲን ዜናማርቆስ ባንቴ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በአዲሱ የትምህርት ዘመን የኒውክሌር ምህንድስና ትምህርት በሁለተኛ ዲግሪ ሊሰጥ ነው።
በሀገሪቷ የኒውክሌር ቴክኖሎጂን እንደ አንድ አማራጭ የኃይል ምንጭ አድርጎ የመጠቀም ዕቅድ በመኖሩ ፕሮግራሙን መስጠት ማስፈለጉ ገልጸዋል።
ዩኒቨርሲቲዉ ትምህርቱን መከታተል የሚፈልጉ ተማሪዎችን እየመዘገበ ሲሆን ለዚህ ትምህርት ብቁ የሚሆኑትም ከዚህ ቀደም በኬሚካል ኢንጅነሪንግ፣ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ፣ በኬሚስትሪ፣ በፊዚክስ እና በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፎች የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸዉ መሆናቸዉን ተናግረዋል።(ኢፕድ)
