“አውሮጳ እና አሜሪካ ስምምነት ደረሱ

Date:

የጀርመን መራሔ መንግሥት ፍሬድሪሽ ሜርዝ በአውሮጳ ህብረት እና በዩናይትድ ስቴትስ መካከል ያለውን የቀረጥ ውዝግብ ለመፍታት የተደረሰውን ስምምነት በደስታ ተቀበሉ።

በአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ኡርዙላ ፎን ዴር ላይን እና በዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ መካከል የተደረሰውን የንግድ ስምምነት ተከትሎ “አውሮጳ እና አሜሪካ ስምምነት ላይ መድረሳቸው

በትራንስ አትላንቲክ የንግድ ግንኙነት ላይ አላስፈላጊ ነገሮች እንዳይባባሱ ጥሩ ነው” ሲሉ ሜርዝ እሁድ አመሻሽ ላይ ተናግረዋል።

ጀርመናዊቷ የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ፎን ዴር ላይን  ትናንት እሁድ ነበር ከፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለአንድ ሰአት ከፈጀ ስብሰባ በኋላ ከስምምነት የደረሱት።

በስምምነቱ መሠረት ዩናይትድ ስቴትስ በአውሮጳ ህብረት ምርቶች ላይ 15 በመቶ ቀረጥ መጣል ትችላለች።

ይህም ትራምፕ ከፈለጉት እና ለወራት በአሜሪካ እና በአውሮጳ ህብረት መካከል ውዝግብ ከፈጠረው 30 በመቶ ቀረጥ በግማሽ ያነሰ ነው።

ስምምነቱ የተደረሰው የትራምፕ አስተዳደር የጣለውን ከፍተኛ ቀረጥ ተግባራዊ ሊያደርግ ያስቀመጠው ቀነ ገደብ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት ነው።

ምንም እንኳን የጀርመን መራሔ መንግሥት ሜርዝ ስምምነቱን ቢያወድሱም የጀርመን የውጭ ንግድ ማህበራት ስምምነቱን “የሚያም” ብለውታል።

ትራምፕ ስምምነቱን “ለሁሉም ባለድርሻ አካላት ጥሩ ነው” ሲሉ አድንቀዋል። እንደ ኡርዙላ ፎን ዴር ላይን ገለፃ እንደ አልኮል ባሉ የተወሰኑ ምርቶች ላይ ምንም አይነት ቀረጥ የማይጣልበት ሁኔታ እንዲኖር ቀጣይ ድርድር ይኖራል።

አሁን የተደረሰው ስምምነት ተግባራዊ መሆን እንዲችል 27ቱ የአውሮጳ ህብረት አባል ሀገራት ስምምነቱን ማፅደቅ ይኖርባቸዋል።

DW Amharic

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በከባድ ሙስና የተከሰሱትን 4 ተከሳሾችን፤ ፖሊስ ፍርድ ቤት ማቅረብ ሳይችል ቀረ

በከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸው በፖሊስ የ'ይፈለጋሉ" ማስታወቂያ የወጣባቸው...

ስለመካከለኛው ምስራቅ አዲስ ውጥረት እስካሁን የታወቁ ጉዳዮች

🔸 ትላንት ምሽት ከኢራን ግዛት የተተኮሰ የሮኬት ጥቃት በሰሜናዊ...

የወንጀል ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕጉ በጋዜጣ እስኪታተም ረቂቅ ሰነዶችን ከመጠቀም እንዲቆጠብ የፍትሕ ሚኒስቴር አሳሰበ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. የፍትሕ ሚኒስቴር አዲሱ የወንጀል ሕግ ሥነ-ሥርዓትና ማስረጃ ሕግ...

ፔንታጎን የእስራኤል ስለላ እንደሚያሳስበው ተገለጸ

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ፔንታጎን እስራኤል ከፍተኛ ልዑኮችን ጨምሮ የአሜሪካ...