አየር መንገዱ በአፍሪካ የመጀመሪያዉን የጭነት አውሮፕላኖችን ሊረከብ ነዉ

Date:

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአየርላንዱ AerCap ኩባንያ ጋር በተደረገ የሊዝ (ኪራይ) ስምምነት፣ ሁለት በሰው ሰራሽ መንገድ ወደ ጭነት አገልግሎት የተለወጡ ቦይንግ 777-300ER አውሮፕላኖችን ሊረከብ ነው። አውሮፕላኖቹ እ.ኤ.አ. በ2028 ሁለተኛው ሩብ ዓመት ላይ ለአየር መንገዱ ይረከባሉ

AerCap የእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ (IAI) ከሚያከናውነው መንታ ሞተር ያላቸውን አውሮፕላኖች ወደ ጭነት አውሮፕላን የመለወጥ መርሃ ግብር አጋር ነው

777-300ERSF ተብሎ የተሰየመው ይህ የጭነት አውሮፕላን፣ ባለፈው ዓመት ከአሜሪካ እና ከእስራኤል የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያገኘ ሲሆን፣ በመቀጠልም በካሊታ ኤር በኩል ወደ አገልግሎት ገብቷል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ እነዚህን የተቀየሩ ጄቶች ለመረከብ ያደረገው ስምምነት፣ አውሮፕላኑ በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ስራ እንዲጀምር ያደርገዋል

“እነዚህ አውሮፕላኖች የጭነት አቅማችንን እና ብቃታችንን በከፍተኛ ደረጃ የሚያሳድጉ ሲሆን፣ በቀጠናው ያለውን የንግድ እንቅስቃሴም ያፋጥናሉ” ሲሉ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።

የእስራኤል ኤሮስፔስ ኢንዱስትሪ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ከአምስት ዓመታት በፊት የአውሮፕላን ለውጥ ስራ ትብብር ስምምነት መፈራረሙ ይታወሳል። ይህም በአዲስ አበባ በሚገኘው የአየር መንገዱ ጥገና ማዕከል የ767-300ER አውሮፕላኖችን የማስተካከያ ስራ የሚያካትት ነበር። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሶስት 767 አውሮፕላኖቹን ለመለወጥ በማቀድ የትብብሩ የመጀመሪያ ደንበኛ ሆኖ ነበር።

አየር መንገዱ በአሁኑ ወቅት የቦይንግ 777F አውሮፕላኖችን እየተጠቀመ የሚገኝ ሲሆን፣ በ2022 ደግሞ አምስት 777-8 የጭነት አውሮፕላኖችን ለመረከብ የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት ማድረጉ ይታወሳል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...