አዲስ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ኢራን የበለጠ ምላሽ በመስጠት የተራዘመ ጦርነት እንደምታካሂድ አስታወቀች

Date:

ከፍተኛ የኢራን ወታደራዊ ባለሥልጣናት አሜሪካ ሌላ ዙር ጥቃት በአገራቸው ላይ የምትከፍት ከሆነ ከባድ ጥቃት በመሰንዘር ለተራዘመ ጦርነት እየተዘጋጁ መሆናቸውን ተናገሩ።

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ከፍተኛ ባለሥልጣን ራሱል ሳናኢ-ራድ ከአሜሪካ ጋር አዲስ ጦርነት የሚቀሰቀስ ከሆነ ቴህራን “ከዚህ በፊት ከነበረው በጠነከረ ሁኔታ” ምላሽ እንደምትሰጥ አስታውቀዋል።

ፋርስ የተባለው የኢራን ዜና ወኪል እንደዘገበው የአብዮታዊ ዘቡ ጠቅላይ አዛዥ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ጉዳዮች መኮንን የሆኑት ባለሥልጣን “ጠላት በአገር ውስጥ ክፍፍልን በመፍጠር እና የኢኮኖሚ ጫና በማሳደር ተቃውሞዎችን መፍጠር እንደሚችል በማሰብ ጥረት እያደረገ ነው” ብለዋል።

በተጨማሪም የኢራን ሠራዊት ምክትል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም አሊሬዛ ሼክ በበኩላቸው የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ “ለተራዘመ ጦርነት” እና ቀጣይነት ላለው ዘመቻ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

እንዲሁም የኢራን የጦርነት መርኅ ግልጽ ከሆነው የመከላከል አቋም ወደ “ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት እና ማጥቃት” መሸጋገሩን እንዲሁም የበለጠ ሚሳዔል እና ድሮን የማምረት አቅምን ቀጣይነት ላለው ዘመቻ ወሳኝ መሆኑን አመልክተዋል።

1በሳምንታት ውስጥ ይጠናቀቃል የተባለው አሜሪካ በኢራን ላይ የከፈተችው ጦርነት ሞቅ ቀዝቀዝ እያለ ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ በድርድር እንዲያበቃ ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ነው።

    ያጋሩ!

    መጽሔቶች

    በብዛት የተነበቡ

    ተጨማሪ ጽሑፎች
    ተመሳሳይ

    ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት ገለጸች

    ኢራን የአሜሪካን የጦር መርከቦች ዒላማ የማድረግ አቅም እንዳላት የአገሪቱ...

    ከትግራይ ዩኒቨርሲቲ ታጣቂዎች ካልወጡ ተማሪ አንመድብም

    ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል የሚገኙ መቐለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና...

    ኢራን አሜሪካ የጣለችባት ዕገዳ የበለጠ የሚጎዳው ዋሽንግተንን ነው አለች

    አሜሪካ በኢራን ላይ የጣለችው የኢኮኖሚ እና የባሕር እንቅስቃሴ እገዳ...

    ግብጻዊቷ የቴሌቪዥን አዘጋጅ በዕፅ ዝውውር ወንጀል የሞት ፍርድ ተወሰነባት

    የካይሮ የወንጀል ችሎት፤ ዕውቋን የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅ ሳራ ካሊፋን...