አሜሪካ በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ ላልተወሰነ ጊዜ ልታራዝም እንደምትችል አስታወቀች

Date:

አሜሪካ ሐሙስ ዕለት በኢራን ወደቦች ላይ የጣለችውን እገዳ ላልተወሰነ ጊዜ በማራዘም የምጣኔ ሃብት ጫናውን ልታጠናክር አንደምትችል ተናገረች።

አሜሪካ ይህንን ያለችው በሁለቱ አገራት መካከል ይደረጋል ተብሎ የሚጠበቀው ድርድር ባለመሳካቱ ውጥረት ባየለበት እና የዓለም የነዳጅ ዘይት አቅርቦት እየቀነሰ በመጣበት ወቅት ነው።

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር የሆኑት ፒት ሄግሴት ለጋዜጠኞች፣ ጦሩ በኢራን ላይ የተጣለውን እገዳ ለማስቀጠል በቀጣናው መቆየት የሚያስችል አቅም አለው ብለዋል።

በኢራን ወደቦች ላይ የተጣለው እገዳ አገሪቱ ላይ የምጣኔ ሃብት ጫና እየፈጠረ ነው።

“የአሜሪካ የባህር ኃይል እንደዚህ ዓይነት የእግድ እርምጃን ላልተወሰነ ጊዜ ማስቀጠል ይችላል፤ ምክንያቱም ቀደም ሲል እንዳደረግነው ሁሉ መርከቦችን እየቀያየርን ማስገባትና ማስወጣታችንን እንቀጥላለን” ሲሉ ሄግሴት ወደ ፓናማ ባደረጉት ጉዞ ወቅት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ ስኮት ቤሴንት ደግሞ አገራቸው በኢራን ኢኮኖሚ ላይ ተጨማሪ ጉዳት ለማድረስ ማቀዷን ይፋ አድርገዋል።

“በሚቀጥለው ሳምንት ለሚሰጡ ተጨማሪ መግለጫዎች ተዘጋጁ። ምክንያቱም በአንድ አገር ላይ በሚደረግ የኢኮኖሚ ማግለል ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ ዓይነት እርምጃዎችን ልንወስድ ነው” ሲሉ ከኒውስማክስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ወቅት ተናግረዋል።

በሰኔ ወር በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ከፈረሰ ወዲህ ኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም በመዝጋት አሜሪካ ላይ ጫና ለመፍጠር እየሞከረች ነው።

ጦርነቱ ከጀመረበት የካቲት ወር አንስቶ ወሽመጡን ለማቋረጥ የሚሞክሩ መርከቦች ላይ ጥቃት የምትፈጽመው ቴህራን የዓለም የነዳጅ ዋጋ ከፍ እንዲል አስተዋጽኦ አድርጋለች።

ሐሙስ ዕለት ምሽት የአቡዳቢ ብሔራዊ የነዳጅ ኩባንያ ንብረት የሆኑ ሁለት ነዳጅ ጫኝ መርከቦች ጥቃት እንደደረሰባቸው የዩኤኢ ብሔራዊ ዜና ኤጀንሲ ዋም ዘግቧል።

የዩናይትድ አረብ ኤሜሬትስ መንግሥት የኢራንን ጥቃት አውግዟል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጦርነቱን በፍጥነት እንዲቋጩ ከአገር ውስጥ ከፍተኛ ግፊት እየደረሰባቸው ነው።

ትራምፕ፣ አሜሪካ በባህር ወሽመጡ ላይ “ሙሉ ቁጥጥር” እንዳላት በተደጋጋሚ የገለጹ ሲሆን፣ ኢራን ይህንን አስተባብላለች።

ቴሀራን ያስቀመጠቻቸው ቅድመ ሁኔታዎች እስኪሟሉ ድረስ ወሽመጡ ዳግም እንዲከፈት እንደማትፈቅድ አስታውቃለች።

ከቅድመ ሁኔታዎቹ መካከል የኢኮኖሚ ማዕቀቦችን ማንሳት እና የታገዱ የኢራን ሃብቶችን መልቀቅ ይገኙበታል።

ማክሰኞ ዕለት በወሽመጡ በኩል ያለፉ መርከቦች ስምንት ብቻ ናቸው። ከጦርነቱ በፊት ግን በሆርሙዝ በኩል በቀን ከ130 እስከ 140 መርከቦች ያልፉ ነበር።

አሜሪካ በሰኔ ወር አጋማሽ ላይ በኢራን ወደቦች ላይ ጥላ የነበረውን እገዳ አንስታ የነበረ ቢሆንም ጦርነቱ ዳግም ማገርሸቱን ተከትሎ በአገሪቱ ላይ የምጣኔ ሃብት ጫና ለማሳደር በሚል ዳግም ወደ ወደቡ የሚደረግ እንቅስቃሴን አግዳለች።

ዋሺንግተን ቀድመ ሲል ኢራን እና ኦማን በወሽመጡ አስተዳደር ላይ የሚስማሙ ከሆነ እገዳውን አነሳለሁ ብላ ነበር።

BBC

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አቶ ይህንዓለም አቅናው የአማራ ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሆኑ

በኢትዮጵያ በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ እና ከፍተኛ የባለአክስዮኖች ቁጥር ካላቸው...

ማዕቀቦች የኢራንን የኒውክሌር መርሃ-ግብር ቢያደናቅፉም መንግስቱን ሊጥሉ እንደማይችሉ ተገለጸ

ማዕቀቦች የኢራንን ወታደራዊ እና የኒውክሌር እንቅስቃሴዎች አስቸጋሪና ውድ እንዲሆኑ...

የአፍሪካ ሀገራት አዲስ የኢንቨስትመንት ፈንድ ይፋ አደረጉ

በአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደቀነውን ከፍተኛ የብድር ጫና ለማቃለል እና...

ዶናልድ ትራምፕ “በቅርቡ” ሆርሙዝ የአሜሪካ ግዛት አካል እንደሚሆን ተናገሩ

ከኢራን ጋር ያለው ግጭት እየተባባሰ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የአሜሪካው...