” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

Date:



የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።

በዚህም ወቅት አሜሪካ ” ፕሮጀክት ፍሪደም ” በሚል በሆርሙዝ ሰርጥ የሚተላለፉ መርከቦችን ለመጠበቅ እርምጃ እየወሰደች መሆኑን ገልጸዋል። በዚህ እርምጃ ወቅት በመርከቦቿ ላይ ጥቃት ከተፈጸመ ” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” ሲሉ ዝተዋል።

ይህን ያሉት የአሜሪካ ኃይሎች የሆርሙዝ ሰርጥ ለማስከፈት እየወሰዱት ባለው እርምጃ ሰባት የኢራን ” ትንንሽ ጀልባዎችን ” መምታታቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ካስታወቁ በኋላ መሆኑ ተገልጿል።

አሜሪካ የኢራንን ድሮኖችና ሚሳዔሎችን መትታ መጣሏንም አስታውቃለች።

ትራምፕ በጦርነቱ ምክንያት በሆርሙዝ ሰርጥ መተላለፍ ላልቻሉት የንግድ መርከቦቻቸው መንገድ እንዲያስከፍቱ ” በዓለም ዙሪያ ካሉ አገራት ” ቀረበልኝ ባሉት ጥያቄ መሰረት ” ፕሮጀክት ፍሪደም ” የተባለ ዘመቻ ከሰኞ ጀምሮ እያካሄዱ እንደሆኑ አመልክተዋል።

በዚህም የአሜሪካ ኃይሎች የመርከቦቹን ደኅንነት ለመጠበቅ ሆርሙዝ ላይ በመሰማራት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ እንደሚያደርጉ ተገልጿል።

ነገር ግን ኢራን ይህንን የአሜሪካ እርምጃ በመቃወም የአሜሪካ ባሕር ኃይል መርከቦችን እንደምትመታ እየዛተች ነው።

መረጃው ከፎክስ ኒውስ እና ቢቢሲ የተገኘ ነው።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ፑቲን እና ሺ ጂንፒንግ በቻይና ውይይት ያደርጋሉ 

የሩሲያው ፕሬዝዳንት ወደ ቻይና የሚያደርጉትን መጪ ጉብኝት አስመልክቶ የክሬምሊን...

ከምዝገባ ካርድ ባሻገር፦ ለነገው ድምፅ የዛሬው ጥንቃቄ

ግዮን መጽሔት :- የምርጫ ካርድዎን በእጅዎ ይዘዋል? እንኳን ደስ...

በጤና አገልግሎት ማስታወቂያዎች ላይ የሕመምተኞችን ምስክርነት መጠቀም ተከለከለ

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ባወጣው አዲስ መመሪያ መሠረት በኢትዮጵያ ውስጥ...

ሴቶችን በቤት ውስጥ በማገዝ  መልካም ማህበረሰብ መፍጠር ተጀምሯል

በቤት ውስጥ የሚሠሩ ተግባራትን ተከፋፍሎ በመሥራት ሴቶችና እናቶችን መደገፍ...