ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአሜሪካ ፍላጎቶች ካልተሟሉ የከፋ ነገር ይገጥማታል ሲሉ ዛቱ።
ኢራንና አሜሪካ ወደ ድርድሩ መድረክ ከስምንት ወራት በኋላ ቢመለሱም ትራምፕ ወታደራዊ እርምጃን ግምት ውስጥ እያስገቡ ነው።
ከኑክሌር ማብላላት እስከ ሚሳኤል መርሃ ግብር ድረስ ቴህራን የዋሽንግተንን ፍላጎት እንድታሟላ ሪፐብሊካኑ ፍላጎታቸው ሆኗል።
በሌላ በኩል አያቶላዉያኑ ከብሄራዊ ጥቅማችን በተወሰነ መጠንም ቢሆን ዝንፍ አንልም በሚል እየሞገቱ ይገኛል።
ስምምነት ላይ ካልተደረሰ አደገኛ እርምጃ በኢራን ላይ እንደሚወሰድ ትራምፕ ይግለፁ እንጂ በኢራን በኩል ያለው ወታደራዊ ዝግጅትም ስጋት ሆኖባቸዋል።
“ወይ ከስምምነት ላይ እንደርሳለን፤ካልሆነ ግን የሆነ እጅግ ብርቱ ነገር ይኖረናል”ብለዋል ትራምፕ።
ይህ አስተያየት የተሰማው የኢራን የደህንነት ሀላፊ አሊ ላሪጃኒ ከዖማኑ ሱክጣን ቢን ታሪቅ አል-ሰይድ ጋር በድርድሩ ውጤት ላይ እየተመካከሩ ባሉበት ሰዓት ነው።
