
ኢትዮጵያ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ወደ ቻይና እና ሞንጎሊያ ጥራቱና ደኅንነቱ የተረጋገጠ የተቀቀለ ሥጋ በመላክ ከ28 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ማግኘቷን የኢትዮጵያ ግብርና ባለሥልጣን አስታወቀ።
የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ እንደገለጹት፣ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ከሚሌ ኳራንታይን 400 ሺህ የቁም እንስሳት ጤንነታቸው ተረጋግጦ በባለሥልጣኑ ሰርተፍኬት ወደ ውጭ ሀገር በመላክ ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ተገኝቷል።
በተለይም ኢትዮጵያ ለዓረብ ሀገራት ብቻ ስጋ ስትልክ የቆየች ሲሆን፣ በዚህ ዓመት ወደ ቻይና ስጋ መላክ መጀመሯ ትልቅ ስኬት ነው ብለዋል።
በ2016 ዓ.ም. ዓመቱን ሙሉ 300 ሺህ ያህል ከብቶች ወደ ውጭ ተልከው 18 ሚሊዮን ዶላር ብቻ ተገኝቶ እንደነበር አስታውሰው፣ በዚህ ዓመት ግን በግማሽ ዓመት ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ ከብቶች ተልከው ከ28 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን ከፕሬስ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።