እስራኤል በየመንዋ ሰንአ ከተማ በሚገኘው ዋና አየር ማረፍያ ላይ ጥቃት ማደረሷ ተነገረ፡፡
በጥቃቱ አሸባሪ ባለቻቸው አካላት ላይ ጥቃት ማድረሷን እስራኤል አስታውቃለች።
የመን በበኩሏ ጥቃቱ ንፁሀንን ላይ ያነጣጠረ ነው ስትል ከሳለች።
የሰንአ አየር ማረፍያ ዋና ዳይሬክተር ካሊድ አልሸረፋ በ ኤክስ የማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንደገለፁት ለሲቪል አገልግሎት የሚውል በየመን አየር ማረፍያ ባለቤትነት የተያዘ አውሮፕላን በጥቃቱ ሙሉ ለሙሉ እንደወደመ ፅፈዋል።
የእስራኤል የመከላከያ ሚንስቴር ኢስራኤል ካትዝ በበኩላቸው ጥቃቱ የሐውቲ አማፅያንን ኢላማ ያደረገ እንደሆነ መግለጻቸውን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡
ሀገሬ ቲቪ
