ኦቲዝም በህፃናት ላይ የነርቭና የእድገት ክትትል ላይ ከፍተኛ ችግር የሚፈጥር ሲሆን የልጁን ከሰዉ ጋር የሚያደርገዉን ግንኙነትና የመግባባት ችሎታ/ክህሎት የሚጎዳ/የሚቀንስ የሕመም አይነት ነዉ፡፡
ለችግሩ መከሰት የሚያጋልጡ ነገሮች፦
የልጅ ፆታ
- ከሴቶች ይልቅ ወንዶች እስከ አራት ጊዜ እጥፍ ተጋላጭ ናቸዉ፡፡
- በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ከነበረ
- በቤተሰብ ዉስጥ መሰል ችግር ያለበት ልጅ ያላቸዉ ቤተሰቦች ቀጣይ የሚወልዷቸዉ ልጆች ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነዉ፡፡
ያለቀናቸዉ በሚወለዱ ህፃናት ላይ
- የመዉለጃ ጊዜያቸዉ ሳይደርስ ከ26 ሳምንታትና ከዚያ በታች የሚወለዱ ህፃናት ላይ የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነዉ።
የወላጆች እድሜ
- ተጨማሪ ጥናቶች የሚያስፈልግ ቢሆንም እድሜቸዉ ከገፉ ወላጆች የሚወለዱ ህፃናት ከሌሎች አንፃር ችግሩ ሊከሰትባቸዉ ይችላል፡፡
ምልክቶቹ፦
የኦቲዝም ምልክቶችን አንዳንዴ በጨቅላ ህፃናት ላይ ሊታይ ይችላል፡፡ ሌሎች ህፃናት ደግሞ የመጀመሪያ ወራት ወይም ዓመታት ላይ ያለምንም ችግር ያድጉና ድንገት መነጠል ወይም ኃይለኛ መሆን ይታይባቸዋል።
- የአይን ግንኙነት ማድረግ አለመቻል ወይም ትንሽ የአይን ግንኙነት ብቻ ማድረግ፤
- ወላጆች ሲያጫውቶቸው ትንሽ ወይም ምንም ምላሽ አለማሳየት፤
- ተገቢ የሆነ የፊት ገፅታ ለነገሮች አለማሳየት፤ እስከ 15 ወር ድረስ ምንም ቃል አለመናገር፤
- በሁለት አመታቸው ሁለት የቃላት ሐረግ መጠቀም አለመቻል፤
- ስማቸው ሲጠራ አለመዞር ነገር ግን ለሌሎች ድምፆች ምላሽ መስጠት፤
- ንግግር መጀመር ወይም መቀጠል አለመቻል፤
- ተደጋጋሚ ወይም መደበኛ ድርጊቶችን ማዘውተር በቀን ብዙ ጊዜ መደጋገም፤
- ህመም ሲሰማቸው አለማልቀስ፤
- በተወሰነ አካላቸው እንጂ በሙሉ አካል አለመጫወት፤
- ጣት መቀሰር አለመቻል፤
ሕክምናው፦
ኦቲዝምን ሊያድን የሚችል ምንም አይነት ህክምና እስከአሁን የለም፡፡ ነገር ግን ልጅዎ ላይ የሚታዩትን የህመም ምልክቶች በመቀነስ የልጅዎን እድገትና የትምህርት ሁኔታ ማሻሻል ይቻላል፡፡
የመድሐኒት ሕክምና፡-
ዋናዎቹን የህመም ምልክቶች የሚያሻሽል መድሃኒት እስከአሁን ባይገኝም ምልክቶቹን ለመቆጣጠር የሚረዱ የተወሰኑ መድሃኒቶች አሉ፡፡ ለምሳሌ አንታይዲፕሬሳንት የመሣሠሉት በሃኪም ሊታዘዙ ይችላሉ፡፡
የመግባባት ክህሎትና የባህሪ ለዉጥ ህክምናዎች
የልጁን የሚያስቸግሩ ባህሪያቶችን ለመቀነስና አዳዲስ ችሎታዎችን ማስተማር ላይ ትኩረት ያደርጋሉ፡፡ ሌሎቹ ደግሞ ህፃናቱ በማህበራዊ ግንኙነታቸዉ ላይ እንዴት መሆን/ምን መተግበር እንዳለባቸዉ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር እንዴት መግባባት እንደሚችሉ ትኩረት ያደርጋል፡፡
ቤተሰብ ተኮር ሕክምና
ወላጆችና ሌሎች የቤተሰቡ አባላት የልጁን የመግባባት ክህሎት፣ችግሮችን የመፍታት ችሎታ ለማዳበር እንዲሁም በየቀኑ የሚጠቀምበትን የመግባባት ክህሎቱን ለማሳደግ በሚረዳዉ መልክ እንዴት አብረዉ መጫወትና መግባባት እንደሚችሉ ማስተማር ያፈልጋል፡፡ በአጠቃላይ ልጅ ሲጫወት፣ ሲማር፣ ሲያወራ ስጋት ካለ በአፋጣኝ ሐኪም ማማከር ያስፈልጋል። ቀድመው ወይም በፍጥነት እክሎችን ማስተዋል የእድገት ደረጃ ላይ ለውጥ ያመጣል። ስለዚህም ህፃናትን ከጨቅላነት እድሜያቸው ጀምሮ እድገትና ባህሪያቸውን ማስተዋልና መከታተል እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። ይህ መረጃ የኦቲዝም ቀንን አስመልክቶ በዶ/ር ቱሚም ጌታቸው (አጠቃላይ ሀኪም እና ሁለንተናዊ የህጻናት እድገት ባለሞያ) የቀረበ ነው።
ከእርግዝና በፊት መቋረጥ ያለባቸው 4 ጎጂ ልማዶች
ያለሐኪም_ትዛዝ_መድሃኒቶችን_መውሰድ
በእርግዝና ወቅት ማንኛውንም መድሃኒት ከመውሰድሽ በፊት ሃኪም ማማከር አለብሽ ይህም የሚሆነው አንዳንድ መድሃኒቶች ፅንሱ ላይ የማይመለስ ጉዳት ስለምያስከትሉ ነው።
ሲጋራ_ማጨስ
በእርግዝና ወቅት ከሚያጋጥም የተዛባ የደም ዝውውር፣ የአተነፋፈስ ችግር፣ የሳንባ ጉዳት በመጠበቅ ፅንሱ ተገቢውን ደም፣ ምግብ እና ኦክስጅን እንዲያገኝ ለማድረግ ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ ተገቢ ነው ተብሏል፡፡ ይህም መሆን ያለበት ከእርግዝና በፊት፣ በእርግዝና ወቅት እና ከወሊድ በኋላ ሲሆን፥ ካርቦን ሞኖ ኦክሳይድ እና ኒኮቲንን በውስጡ የያዘውን ሲጋራን በመራቅ ለእርግዝና መዘጋጀት ወሳኝ መሆኑ ተመክሯል፡፡
አልኮልን_ወይም_አነቃቂ_ዕፆችን_መጠቀም
አልኮል ከእናት የእንግዴ ልጅ አልፎ በልጅ ወይም በፅንሱ ላይ ጉዳት ያስከትላል ነው የሚለው፡፡ አልኮል መጠጣትን በቅድመ እርግዝና ወቅት ማቆም ካልተቻለ ጎጂ ልማዱ በእርግዝናም ወቅት ቀጥሎ፥ ሽሉ ላይ ተፅዕኖ በማሳደር ከመደበኛው ጊዜ ቀድሞ መወለድን፣ የፅንስ መጨናገፍን፣ የህጻኑን ክብደት መቀነስን እና የእድገት መቀጨጭን ሁሉ ያስከትላል፡፡
ተገቢ_ያልሆነ_አመጋገብ
አንዲት እርጉዝ እናት በእርግዝና ወቅትም ሆነ ከእርግዝና በኋላ ስላለው ተገቢ እና የተመጣጠነ አመጋገቧ ትኩረት ማድረግ ይኖርባታል፡፡ ከፍተኛ የሆነ የሶዲየም እና የስኳር መጠን ያላቸውን ምግቦች፣ በማምከኛ ውስጥ ያልገቡ የስጋ እና ወተት ተዋፅኦዎችን እና በአግባቡ ያልታጠቡ ምግቦችን አለመመገብ፤
