ኢትዮጵያ በ2018 በጀት ዓመት ከቡና ኤክስፖርት 3 ቢሊየን የአሜሪካን ዶላር ለማግኘት የያዘችው ዕቅድ ማሳካቷን የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ አዲሱ አረጋ ገለፁ፡፡
ሚኒስትሩ በባለፈው በጀት ዓመት 2 ነጥብ 65 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ማግኘት ተችሎ የነበረ ሲሆን ይህን ቁጥር አመት ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ ማሻሻል የተቻለው መንግስት ለዘርፉ በሰጠው ትኩረት የቡናውን ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን የሚያሳድጉ ስራዎች መሰራታቸው በተለይም ለቡና ምርት ጥራት ትኩረት መደረጉ ለዕቅድ ስኬት ድርሻው ከፍተኛ መሆኑን ገለጸዋል።
ይህንንም እቅድ ከግብ ለማድረስ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ላበረከታችሁ የቡናው ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ምስጋና አቀቧል፡፡
