ሂዝቦላህ የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ ማድረጉ ሰገለጽ፥ የእስራኤል ከባድ ጥቃቶች ተፋፍመው መቀጠላቸው ተነገረ።
የሊባኖሱ ሄዝቦላህ በእስራኤል እና በሊባኖስ የተደረሰውን የተኩስ አቁም ስምምነት ውድቅ ሲያደርግ የእስራኤል ከባድ ጥቃቶች ተፋፍመው መቀጠላቸው ተነግሯል።
በኢራን የሚደገፈው የሄዝቦላህ ዋና አዛዥ ናኢም ቃሲም በሰጡት መግለጫ፥ ” ድርድሩ ለሊባኖስ ከንቱ እና አዋራጅ” ነበር ሲሉ ተችተዋል።
ለይስሙላ የተደረገ ሲሉም የተኩስ አቁም ስምምነቱን ውድቅ አድርገውታል።
እስራኤል በሊባኖስ ጥቃትና ድብደባዋን እስከቀጠለች ድረስ ሰሜናዊ እስራኤል የተፋላሚዎች ኢላማ ትሆናለች ሲሉም አስጠንቅቀዋል ዋና አዛዡ ቃሲም።
የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ (IRGC) እስራኤል ከሊባኖስ ግዛት እስክትወጣ ድረስ “በአካባቢው ሰላም አይኖርም” ሲል በቴህራን እና በዋሽንግተን መካከል የተደረገው ስምምነት በዋናነት በሊባኖስ ያለውን ግጭት ማቆምን ያካትታል ሲል አሳስቧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በአሜሪካ አደራዳሪነት በሊባኖስ እና በእስራኤል ባለስልጣናት መካከል በዋሽንግተን ዲሲ የተደረሰው የተኩስ አቁም በቀጠለበት፥ እስራኤል ከባድ ጥቃቶችን በመላው ሊባኖስ አጠናክራ መቀጠሏ ተነግሯል።
ከመጋቢት 2 ጀምሮ እስራኤል በሊባኖስ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 3ሺ 526 ሰዎች ሲገደሉ፥ 10ሺ 733 ቆስለዋል ሲል የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።
ዘገባው የአልጀዚራና ቢቢሲ ነው።
