ከ70 ግራም በታች ሲሸጡ  በተገኙ ከ72 በላይ  ዳቦ ቤቶች ላይ ሕጋዊ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስአበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

Date:

በንግድ ቢሮዉ ከተተመነዉ 70 ግራም በታች ሲሸጡ የተገኙ ከ72 በላይ ዳቦ ቤቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ያስታወቀ ሲሆን የሚደረገዉ ቁጥጥር እንደሚቀጥል ገልጿል ፡

እርምጃ ከተወሰደባቸዉ 72 ዳቦ ቤቶች ዉስጥ 65ቱ ዳቦ ቤቶች ወደ ህጋዊነት እንዲመለሱ መደረጉን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የህጋዊ ስነ ልክ ቡድን መሪ ደረጀ በቀለ ለጣቢያችን ተናግረዋል ፡፡

ዳቦ ከመሰረታዊ ድጎሞ ሸቀጦች ዉጭ መሆኑን ያስታወሱት  የህጋዊ ስነ ልክ ቡድን መሪዉ  ንግድ ቢሮዉ ዳቦ ቤቶች በተለጠፈዉ ዋጋ እና ግራም እየሸጡ ነዉ  የሚለዉን  ብቻ ክትትል እያደረገ መሆኑን ገልፀዋል ፡፡

ንግድ ቢሮዉ በክትትል እና በቁጥጥር ወቅት ከለጠፉት የዳቦ መሸጫ ዋጋ በላይ እና ከተተመነዉ ግራም በታች መጠን ያለዉ ምርት በሚሸጡ ዳቦ ቤቶች ላይ ከፅሁፍ እስከ ንግድ ፍቃድ መሰረዝ እርምጃ የሚወስድበት አሰራር ስለመኖሩአቶ ደረጀ በቀለ አስታዉቀዋል ፡፡

ዳቦ ቤቶች ከለጠፉት ከዋጋ ዝርዝር በላይ ሲሸጡ እንዲሁም ግራም አጉድለዉ ሲገኙ ህብረተሰቡ በነፃ ስልክ ቁጥር 85 88 ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ተነግሯል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ትራምፕ ከኢራን ጋር የተስማሙባቸውን ነጥቦች ከአርብ በፊት ይፋ ሊያደርጉ ይችላሉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ጦርነቱን ለማቆም የተስማሙባቸውን...

‹‹ሃገረ ትግራይ›› በዘመናት መነፅር ሲታይ

(አጭርዳሰሳ) በወሰንሰገድ ገ/ኪዳን (ጋዜጠኛ) የመጽሐፉርዕስ፡- ሃገረ ትግራይ የመጽሐፉ ዓይነት፡-...

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...