ከ80 ሺሕ በላይ ለሚሆኑ የሁለተኛ ደረጃ መምህራን በክረምት ስልጠና ሊሰጥ ነው

Date:

የመምህራን የብቃት ማነስ ለማሻሻል በክረምት ወቅት የ120 ሰዓት ስልጠና ለሁለተኛ ደረጃ መምህራን ስልጠና ሊሰጥ መሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሙሉቀን ንጋቱ ለአሐዱ እንደተናገሩት፤ በኢትዮጵያ ለትምህርት ሥርዓቱ መጓደል የመምህራን የብቃት ማነስ እንደ ዋና ምክንያት ይነሳል፡፡

ይህን ለማሻሻል ትምህርት ሚኒስተር ከ2016 ክረምት ጀምሮ መምህራን የአቅም ማሻሻያ እንዲወስዱ ሲደርግ  መቆየቱን መሪ ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

በዚህም መሠረት በባለፈው ዓመት ለሁለተኛ ደረጃ ማህበራዊ ሳይንስ እና ሂሳብ መምህራን ውስጥ 60 ሺሕ መምህራን ስልጠናውን ይወስዳሉ ተብሎ በእቅድ የተያዘ ቢሆንም፤ 52 ሺሕ የሚሆኑት መምህራን የአቅም ማሻሻያውን ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን ገልጸዋል፡፡

አክለውም በአሁኑ ዓመት 80 ሺሕ ሁለተኛ ደረጃ መምህራን ለማሰልጠን እቅድ መያዘኑን የተናገሩ ሲሆን፤ “በሁሉንም የትምህርት መስኮች በሚሰተምሩት የትምህርት አይነት መሠረት ስልጠና ይሰጣል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚሰጥ ሲሆን፤ ለ120 ሰዓት እና መምህራን በሚሰጡት ትምህርት መስክ ላይ ከባድ የሆኑት በመምረጥ የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

“ትምህርት ሚኒስቴር ለትምህርት ሥርዓቱ መጓደል እና የጥራቱን ጉዳይ ለመቅረፍ እየሰራ ነው” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...