Home ልዩ ልዩ ዜና ካናል ፕላስ ከታህሣሥ 22 ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ አስታወቀ

ካናል ፕላስ ከታህሣሥ 22 ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ አስታወቀ

ካናል ፕላስ ከታህሣሥ 22 ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ አስታወቀ

የፈረንሳዩ ሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ካናል ፕላስ በኢትዮጵያ ከታህሣሥ 22/04/2017 ዓ.ም ጀምሮ ስርጭቱን እንደሚያቋርጥ አስታወቀ። ካናል ፕላስ በማህበራዊ ትስስር ገፁ “የፕሮግራም ስርጭታችንን ታህሳስ 22 2017 ስለምናቋርጥ የደንበኝነት እድሳት እስከ ጥቅምት 21/2017 ድረስ ይቆያል” ብሏል። በተጨማሪም ቴሌቪዥን ጣቢያው “ለነበረንም ቆይታ በድጋሚ ከልብ እናመሰግናለን” በማለት ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ ካናል ፕላስ እንደሚታወቀው በኢትዮጵያ ከስታር ታይምስ እና ዲ ኤስ ቲቪ ቀጥሎ ሶስተኛው የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናል ነበር።