ትናንት ምሽት በኮንፍረንስ ሊግ ፍጻሜ የስፔኑን ራዮ ቫልካኖን 1-0 በሆነ ውጤት በማሸነፍ በታሪካቸው የመጀመሪያውን የአውሮፓ ዋንጫ አነሱ።
ለብዙ ዓመታት በደረጃ ሰንጠረዥ ግርጌ ላል ከሊጉ ላለመውረድ ሲፋለሙ የቆዩት ፓላሶች በኦሊቨር ግላስነር መሪነት ፍጹም የተለየ ቡድን ሆኗል። በዚህ ውድድርም ፊዮረንቲናን እና ሻካታር ዶኔትስክ ያሉ ጠንካራ ቡድኖችን አሸንፈው ወደ ፍጻሜው ደርሰዋል።
በፍጻሜው ጨዋታ የድሉን ጎል ያስቆጠረው ጃን ፊሊፕ ማቴታ ነበር። ይህ ጎል የሰለረስት ፓርክ ደጋፊዎችን ወደ እብደት ደስታ አስገባ።
🗣️ ኦሊቨር ግላስነር “ይህ ለክለቡ እና ለደጋፊዎቹ የማይረሳ ሌሊት ነው” ብሎ ተናግሯል።
ማቴታም በበኩሉ “ይህን ዋንጫ ለደጋፊዎቻችን አሸንፈናል” ብሎ በደስታ ተናግሯል።
ክሪስታል ፓላስ አሁን ከወራጅ ቀጠና ቡድንነት ወደ ዩሮፕያን መድረክ የተሳካ ጉዞ ተቀይሯል
