እሺ ምን እናድርግ?
አርሲ ብቻ ሳይሆን ኦርቶዶክሳዊነት ወንጀል የሆነባቸው አካባቢዎች ላይ አስቸኳይ፣ መካከለኛና የረጅም ጊዜ መፍትሔ ይፈልጋሉ።
አባቶቻችን ከመግለጫ በተጨማሪ አስበው ዘላቂ መፍትሔ ቀይሰው ይመሩናል ብለን ተስፋ እናድርግ።
ጊዜ የማይሰጥ ጉዳይ ግን አለብን።
የሞቱትን አስበን የምናለቅሰውን የምናዝነውን ገታ አድርገን የተረፉትን ማሰብ አለብን። ወላጆቸእ ጧሪ ልጆቻቸውን ተነጥቀዋል፤ ልጆች መጠጊያ ወላጆቻቸውን አጥተዋል፤ ቤት ንብረታቸው አመድ ሁኗል።
እንኳን ማደሪያ መቆሚያ ምድር ተነፍገዋል።
እህላቸው ተቃጥሏል።
ስለዚህ አስቸኳይ የሰባዊነት ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።
ማኅበረ ቅዱሳን ባለፉት ከ10 ዓመታት በላይ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋ ለተጎዱት ቀድሞ ደርሷል።
በተለይም በኦሮምያ፣ በአማራ፤ ትግራይ እና አፋር ክልሎች ሃይማኖት ሳይለይ የሰበሰበውን አከፋፍሏል።
በአርሲ ብቻ ባለፉት 3 ዓመታት መግቢያ ሲያገኝ ተመላልሶ አለሁ ለማለት ሞክፘል። ችግሩ እሱ አቋቁሞ ሲመለስ ጠላት እየተከተለ ይንዳል።
አሁንም በአርሲና መሰል አካባቢዎች ፈጥነን እንድረስ በማለት እርዳታ እየሰበሰበ ይገኛል።
የቁጭታችን ትንሹ መገለጫ የተረፉትንም አለሁ ብሎ ማጽናናት ነው።
🔷አለሁ እኔ ለወገኔ🔷
ክርስቲያናዊና ወገናዊ ድጋፍ ለማድረግ በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
👇👇👇
CBE – 1000309803648
Ahadu – 0025393810901
Wegagen – 0837331610101
Abysinia – 37235458
Awash – 01329817420400
Dashen- 5171156335011
Telebir 0975005994
Wegen Fund https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም ይችላሉ።
ለበለጠ መረጃ
• 0943000403 / 0962171717/0966636363
🔷ያደረጉትን ድጋፍ🔷
👇👇👇 https://t.me/ArsiSupport ይላኩልን።
