ወደ ብልጥግናም ወደ ተቃዋሚው ፍላጎት ሳትወስዱ አንብቡኝ

Date:

በኢትዮ ኤርትራ ጉዳይ በተለይም የባህር በር ጉዳይ በቅንነት ኢትዮጵያ ይገባታል ብዬ የማምንበት ነው።

ከዚህ ቀደም እንደጻፍኩት የኢትዮጵያ ህዝብ የኤርትራ መገንጠልን ሰማ እንጂ የወሰነው ጉዳይ የለም። መለስና ኢሳያስ ናቸው ዋና ወሳኞቹ።

ይኼ የሽርክና ውሳኔም ለትንሿ አገር ኤርትራ ወደ 1000 ኪ.ሜ የሚጠጋ የባህር በር ሰጥቶ ብዙ ህዝብ ያላትን ኢትዮጵያን ከባህሩም ከወደቡም የገፋ ኢ-ፍትሃዊ ውሳኔ ነው።

መለስ የመራው የሽግግር መንግስት መገንጠሉን እሽ ይደግፍ እንበል ግን የኢትዮጵያን ታሪካዊ ወደብ አሳልፎ የሰጠበት እብደት ግን የሚያስተዛዝብ ነው።

በዛሬው ዜና መንግስት የኤርትራን የአገርነት ዕውቅና ሊነፍግ ዳርዳር እያለ ይመስላል። ይኼ ለኤርትራ ጥሩ አይመስለኝም። ስለዚህ በዚህም በዚያም በኩል ከመፎከር ሰከን ብሎ ያለ መገፋፋት ኢትዮጵያ የባህር በር የምታገኝበትን መንገዶ ኢሱ ጭሱ ቢያስብበት ጥሩ ነው።

ዳንኤል ተፈራ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 1 2018 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

በኢትዮጵያ ነፃ ኘሬስ ከ25 ዓመት በላይአገልግለናል !!! -የአርበኞች አደራና የትውልዱ...

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...