የህወሓትን መሰረዝ ተከትሎ የአፍሪካ ህብረትለፀጥታ ምክር ቤት አስቸኳይ ስብሰባ ጠየቀ

Date:

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ህወሓትን “ሕገወጥ የፖለቲካ ፓርቲ” ብሎ መሰረዙን ተከትሎ፣ የአፍሪካ ህብረት ለፀጥታ ምክር ቤቱ የአስቸኳይ ስብሰባ ጥሪ አቀረበ።

ህብረቱ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት አደጋ ላይ መውደቁን በመግለጽ፣ ሁኔታው ወደ ከፋ ግጭት ከማምራቱ በፊት በአስቸኳይ መፍትሄ እንዲፈለግ አሳስቧል።

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሰብሳቢ ክቡር ማህሙድ አሊ ዩሱፍ ለምክር ቤቱ በላኩት ደብዳቤ፤ የኢብም ውሳኔ የሰላም ስምምነቱን በግልጽ የሚፃረርና በሰሜን ኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የተደረገውን ጥረት የሚያደናቅፍ ነው ብለዋል።

ህብረቱ፤ ምክር ቤቱ በአስቸኳይ በመሰብሰብ በጉዳዩ ላይ እንዲወያይና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአህጉሪቱን የርስ በርስ ንግድ ልውውጥ 250 ቢሊዮን ዶላር ለማድረስ ታቀደ

የአፍሪካ አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና ዋና ፀሐፊ ዋምኬሌ ሜኔ...

በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦች ክፍያ መፈጸም አይጠበቅባቸውም

አሜሪካ እና ኢራን በተስማሙበት የመግባቢያ ሰነድ መሠረት በሆርሙዝ ወሽመጥ...

እስራኤል ጦሯ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አስታወቀች

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትዝ እንደተናገሩት፤ በአሜሪካ እና በኢራን...

ኧረ ፋታ ስጡን?!

መንግስት ግን" ምን ሁኑ ?" ሊለን ነው :: አጀንዳ...