የህግ ታራሚ ወላጆች የቅርብ ቤተሰብ እያላቸው የቅጣት ማቅለያ ይደረግልናል በሚል በሃሰተኛ ምስክር ከልጆቻቸው ጋር ማረሚያ እንደሚገቡ ተገለፀ

Date:

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በወላጆቻቸው ጥፋት ምክንያት አብረዋቸው ማረሚያ ለሚገቡት ህፃናት የሚደረገውን ድጋፍ ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብሏል፡፡

የክስ ማቅለያ ይደረግልናል በሚል በሃሰተኛ ምስክር ሁለትና ከዛ በላይ ልጆቻቸውን ይዘው ማረመያ የሚገቡ ወላጆች መበራከት ለህፃናቱ ልዩ ክትትል ለማድረግ በሚሰራው ስራ ላይ ተግዳሮት እየፈጠረ መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ይህንን በተመለከተ ለብቻው የተቀመጠ መብትና ድንጋጌ አለመኖሩ ለስራው ተግዳሮት እንደፈጠረበት ለጣቢያችን ገልጿል::

ለህፃናቱ ለብቻ የተመደበላቸው በጀት ካለመኖሩም በተጨማሪ የህግ ክፍተትም እንዳለ የተናገሩት በሚንስቴሩ የህፃናት መብት ጥበቃ መሪ ስራ አስፈፃሚ ዘቢደር ቦጋለ፤ አሰራሩን ለማሻሻል እየተሰራ ነው ብለዋል።

የህፃናቱን የመብት ድንጋጌን ተከትሎ መፍትሔ እንዲያገኝ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

ህፃናቱ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙ ለሚመለከታቸው አካላት ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ እየተሰራ መሆኑንና መብታቸውን በማስጠበቁ ረገድ የቁጥጥር ስራዎችም እየተሰሩ እንዳሉ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጅ በቁጥጥር ሂደቱ እስካሁን ተጠያቂ የተደረገ ማረሚያ ቤት እንደሌለ ነው ያስታወቁት።

menahriaFm

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ከሌ/ጄነራል ታደሰ ወረደ የተላለፈ ጥሪ

በክልላችን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እያደገ የመጣው የተሳሳተ ስሌት የወለደው...

በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ በከባድ መሳሪያዎች የታገዘ  የተኩስ ልውውጥ ተካሄደ

ለዓለም የንግድ ሰንሰለት እጅግ ስትራቴጂካዊ በሆነው የሆርሙዝ ባህረ ወሽመጥ...

የሲ.ኤን.ኤን መስራች ቴድ ተርነር ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

የዓለማችን ግዙፍ የዜና አውታር ሲኤንኤን መስራች ቴድ ተርነር በ87...

የኢትዮጵያ አጠቃላይ ብድር 51.8 ቢሊዮን ዶላር መድረሱ ይፋ ሆኗል

ኢትዮጵያ  በድጋፍ መልክ ከአሜሪካ በየዓመቱ  በመንግስት በኩል ፈሰስ የሚደረግ...