የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሰናል-ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል

Date:

ሐምሌ 12/2018 ዓ.ም በመቀሌ ህዝቡን እና አመራሩን ሰብስበው አወያይተዋል።
።
የትግራይ ህዝብ ጭቆናን የመሸከም ታሪክ የለውም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፤ ይልቁንም መብቶቹ ለማረጋገጥ በመደራጀት ታግሏል፣ መብቶቹን አስከብሯል እንዲሁም የሌሎች ብሔረሰቦችን መብቶች አክብሮ የመጣ ህዝብ ነው ብለዋል።

ለ17 ዓመታት በተደረገው የትጥቅ ትግል ውስጥ የትግራይ ህዝብ ከባድ መስዋእትነት በመክፈል አንባገነኑ የደርግ ስርዓት መደምሰሱን ያወሱት ዶክተር ደብረፅዮን፤ በአንባገነኑ መቃብር በሃገር ደረጃ ሰላም፣ ልማትና የዴሞክራሲ ግንባታ ማረጋገጡን ጠቅሷል፡፡

ሆኖም፣ ይህንን መቀበል ያልቻሉ ሐይሎች ጊዜና አጋጣሚውን በመጠበቅ፣ የትግራይን ህዝብ ከምድረገፅ ለማጥፋት በህዝባችን ላይ ጀኖሳይድ ፈፅሟል ያሉት ፕረዝዳንቱ፤  የትግራይ ህዝብ አንድነቱ በመጠበቅ ልህልውናው በከፈለው መስዋዕትነት ጭቆናን እና ህልውናውን ለማጥፋት ለመጣው ሐይል የማይቀበል መሆኑ በዓለም አደባባይ ያስመሰከረ እንደሆነ ጠቅሷል፡፡ 

የፕሪቶሪያው ስምምነት ሲፈረም፤ የትግራይ ሉዓላዊነት ለማረጋገጥ፣ ተፈናቃዮችን ለመመለስ እና ልማትን ለማረጋገጥ ከፍተኛ ተስፋ አድርገን ነበር።

ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፤የፌደራል መንግሥቱ በታቀደ ሁኔታ ትግራይን ዳግም ወደ ከበባና ክልከላ በማስገባት ለዳግም ጀኖሳይድ እየተዘጋጀ እንደሚገኝ አብራርቷል፡፡

እንደ ትግራይ፣ ለሰላም ስንል ከፍተኛ ትዕግስትና መስዋዕትነት እየከፈልን ነው፤ ይሁን እኛ ብቻ ሰላም ስለ ፈለግን ሊሳካልን አልቻለም ያሉት ዶ/ር ደብረፅዮን፤ አንድነታችን አጠናክረን የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄዎች ማረጋገጥ ብቸኛ መፍትሔ ሆኖ መገኘቱ። ተናግሯል፡፡

አሁን ባለንበት ሁኔታ መቀጠል አንችልም ያሉ ሲሆን እንደህዝብ የመከተ ዓቅሞቻችን በማደራጀት ህልውናችን ለማረጋገጥ በምንወስንበት ምዕራፍ ላይ እንገኛለን ብሏል፡፡


የፌደራል መንግስቱ ለሰላም በፍጹም ዝግጁ አይደለም፤ ስለዚህ ብሔራዊ ክብራችንና ሉዓላዊነታችንን ለመመለስ እንዲሁም የተፈናቀሉ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋም ትግላችንን ወደ ተጨባጭና ውጤታማ ደረጃ ማሸጋገር ይገባናል ብሏል፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አሜሪካ ለኢራን ከፍተኛ ባለሥልጣን ደብዳቤ ላከች

የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ለኢራን ብሔራዊ ደኅንነት ምክር...

ዓመታዊ ግብርን ሙሉ በሙሉ በኦንላይን ማሳወቅና መክፈል የሚያስችል አዲስ አሰራር ተዘረጋች

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ እንዳስታወቀው፣ ከእንግዲህ የደረጃ «ሀ» ግብር...

62ኛው የባህል ማዕከል ምሽት አንጋፋዋን ጋዜጠኛ የመዓዛ ብሩን ዘክሯል

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል፥ በኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙኃን ታሪክ...

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ሀኪም ቁጥር አራት ብቻ ናቸው

በኢትዮጵያ ውስጥ የህፃናት የአዕምሮ ህክምና አገልግሎት በሰፊው እንደሌለ እና...