የሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የዘርፉን ተዓማኒነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን ገለጸ

Date:

​​በኢትዮጵያ ውስጥ ከ3 ሺህ በላይ የሪል ስቴት አልሚዎች እንዳሉ ቢገመትም በማህበር የታቀፉት 100 ያህሉ ብቻ መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን ይህን ክፍተት ለመሙላትና የዘርፉን ችግሮች በጋራ ለመፍታት የሚያስችል የቀጠናዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ሪል ስቴት አልሚዎች ማህበር የተመሰረተበትን አንደኛ ዓመት በማስመልከት ባከናወነው በዚህ ጉባኤ ላይ በዘርፉ የሚታዩ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ ክፍተቶችን ከመንግስት ጋር በመነጋገር ለማሻሻል ግብ መቀመጡ ተመላክቷል።

​የማህበሩ የፖሊሲ ጥናትና አድቮኬሲ ክፍል ሃላፊ አቶ ሲሳይ ዘነበ እንደገለጹት ማህበሩ የአባላቱን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥና የግንባታ ግብዓቶችን በጋራ ለማቅረብ እየሰራ ሲሆን አሁን የተካሄደው የምስራቅ አፍሪካ ሪል ስቴት ቀጠናዊ ጉባኤም በየዓመቱ ለሚካሄደው አህጉራዊ ኮንፈረንስ እንደ መንደርደሪያ የሚያገለግል ነው።

​በሌላ በኩል የማህበሩ የቦርድ አባልና የቴምር ሪል ስቴት ማኔጂንግ ዳይሬክተር አቶ ጃፈር መሐመድ በዘርፉ የጠፋውን ተዓማኒነት ለመመለስና ከመስመር የወጡ አሰራሮችን ለማስተካከል በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

ማህበሩ ከንግድ ምክር ቤት ጋር በመተባበር የግልግል ዳኝነት በማቋቋም የቀድሞ ቅሬታዎችን ለመፍታት እየሞከረ ሲሆን ደንበኞች በማስታወቂያ ጋጋታ ሳይታለሉ የአልሚዎችን ታሪክና አቅም አይተው እንዲገዙ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተከናወነ ይገኛል።

​የቤት ዋጋን ስታንዳርድ ለማስያዝ የጥናት ስራዎች እየተሰሩ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ጃፈር ወደፊት የግንባታ ጊዜንና ጥራትን የሚያረጋግጡ የመንግስት ህጎች ሲጸድቁ በዘርፉ የሚታየው መዘግየትና አለመተማመን እንደሚቀረፍ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

በመጨረሻም አልሚዎች ወደ ማህበሩ በመቀላቀል ለሀገር ኢኮኖሚና ለዘርፉ እድገት የበኩላቸውን እንዲወጡ በውይይቱ መድረክ ላይ ጥሪ ቀርቧል።

getutemesgen #getu #ጌጡ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

በኬንያ የመንገደኞች አውሮፕላን ከመስመሩ ወጥቶ ተከሰከሰ

ዛሬ ረፋድ ላይ በኬንያ ማንዴራ የአውሮፕላን ማረፊያ አንድ...

አቶ ጀማል አህመድ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨማሪ 26 ሚሊየን ብር ሰጡ

አቶ ጀማል አህመድ ባሳለፍነው ወር ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ  ከሰጠው...

“የቻይና-አፍሪካ የምርምር ማዕከል”በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሊከፈት ነው

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከቻይና-አፍሪካ ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር "የቻይና-አፍሪካ የምርምር...

በኢትዮጵያ በማሳደጊያ ተቋማት የሚገኙ ሕፃናት ቁጥር ወደ 12 ሺሕ ዝቅ አለ

በኢትዮጵያ በተለያዩ የሕፃናት ማሳደጊያ ተቋማት ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት...