የሱዳን ፍርድ ቤት የአር ኤስ ኤፍ መሪን በሌሉበት የሞት ፍርድ ወሰነባቸው

Date:

የሱዳን ፀረ-ሽብርተኝነት ፍርድ ቤት የፈጣን ድጋፍ ሰጪ ኃይሎች (አር ኤስ ኤፍ) መሪ መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ፣ በስፋት ሄሜቲ በመባል የሚታወቁት፣ በቀድሞው የምዕራብ ዳርፉር ገዥ ካሚስ አብደላህ አባካር ግድያ ምክንያት እሁድ እለት በሌሉበት የሞት ፍርድ ፈርዶባቸዋል።

በፖርት ሱዳን የሚገኘው የፀረ-ሽብርተኝነት እና የክልል ፍርድ ቤት በሌሉበት የአር ኤስ ኤፍ ምክትል መሪ እና የሄሜቲ ወንድም አብደል ራሂም ሃምዳን ዳጋሎን ጨምሮ እና ሌሎች 14 ተከሳሾች የሞት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

ይህ ውሳኔ በኤፕሪል 2023 በሱዳን ጦር እና በፈጣን ድጋፍ ሰጪ ቡድኑ መካከል ግጭት ከተፈጠረ ወዲህ በአር ኤስ ኤፍ መሪዎች ላይ የተላለፈ የመጀመሪያው የፍርድ ቤት ውሳኔ ነው።

ፍርድ ቤቱ ተከሳሾቹን በጦር ወንጀሎች፣ በሰብአዊነት ላይ በሚፈጸሙ ወንጀሎች፣ የዘር ማጥፋት ፣ በሰዎች እና በንብረት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀሎችን ጨምሮ በተለያዩ ክሶች ጥፋተኛ አድርጎባቸዋል።ሄሜቲን ወንጀሎቹን በማቀድ እና በመሳተፍ ተጠያቂ አድርጓቸዋል።

ከሌሎቹ ተከሳሾች መካከል አልጎኒ ሃምዳን ዳግሎ ሙሳ፣ ሌላው የሄሜቲ ወንድም አል-ቁኒ በመባል የሚታወቀው ሲሆን የምዕራብ ዳርፉር የአር ኤስ ኤፍ አዛዥ አብደል ራህማን ጁማ ይገኙበታል።

በምዕራብ ዳርፉር ዋና ከተማ ኤል ጂንያና ውስጥ አርኤስኤፍ በሲቪሎች ላይ ጥቃት ፈጽሟል ሲል የሱዳን ጦር ከሷል። ጦሩ አክሎም ቡድኑ የዳርፉን ገዢ ገድሎ አስከሬኑን ቆርጦ እንደጣለ ከሷል፣ አር ኤስ ኤፍ በወቅቱ ክሱን አስተባብሏል።

የሱዳን ባለስልጣናት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች አርኤስኤፍን በኤል ጂንያና ውስጥ ሰፊ ጭካኔ ፈጽሟል ሲሉ ከሰዋል፣ ይህም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን መግደል እና በሺዎች የሚቆጠሩ የማሳሊት ማህበረሰብ አባላትን ማፈናቀልን ያካትታል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአንጋፋውን ጋዜጠኛ ድምጽ እንደገና እንስማ

ኑ ጥቂት ድጋፍ አድርገን ተስፋ እናለምልም ‼️ ባለ ወርቃማ ድምጹ...

ግዮን መጽሔት ዛሬ ቅዳሜ መስከረም 9 2019 ዓ.ም ገበያ ላይ ውሏል !!!

-የግዮን እንግዳ አምዳችን :- ‹‹ምንጩና ጸሐፊው በማይታወቅ መረጃ መመራት አደገኛ...

ሸኽ መሃመድ አል አሙዲ ተጨማሪ 40 ሺህ ሠራተኞች እንዲቀጠሩ አቅጣጫ ሰጡ

የMIDROC Investment Group ሊቀመንበር ሼክ መሃመድ ሁሴን አል...

የወርቅ ማዕድን ሠራተኛው ከመገደላቸው በፊት ቤተሰባቸው ከታጣቂዎች ጋር ያደረገው የመጨረሻው የስልክ ምልልስ

ማስጠንቀቂያ፡ ቀጥሎ የሚያነብቡት ታሪክ ሊረብሽዎት ይችላል በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ...