የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሶማሊያ ወታደሮች ስትራቴጂክ ጠቀሜታ ካላት የሶማሊያ ከተማ ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ ሰጡ።
የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ጦር አዛዦች የሶማሊያ ፌደራል መከላከያ ሠራዊት በጌዶ ክልል በሌድ ሀዎ ከተማ ለቀው እንዳወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸው ተሰምቷል።
የኢትዮጵያ ሠራዊት አመራሮች ቁልፍ ወታደራዊ ጠቀሜታ ካላት ኢትዮጵያን ከኬኒያ ከምትዋሰነው በደቡባዊ ሶማሊያ ከምትገኘው በሌድ ሀዎ ከተማ በ72 ሰዓት ውስጥ የሶማሊያ ፌደራል ኃይሎች ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጡትን ከሶማሊያ ምንጮች ተሰምቷል።
በኢትዮጵያ በኩል በከተማዋ የግብጽ ወታደሮች ለመስፈር እየመጢ ናቸው የሚል ሰበብ መቅረቡን ምንጭች ጨምረው ገልጸዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ጧት ከተማዋን ከፌደራል መንግሥት ጋር ግጭት ውስጥ የገባው የጁባ ላንድ አስተዳደር ከባድ መሳሪያዎችን በማስገባት በከተማዋ ዙሪያ መስፈሩ ተገልጿል።
አስተያየት ሰጪዎች የኢትዮጵያ ወታደራዊ አዛዦች ሁለቱ የሶማሊያ ኃይሎች ከተማዋን ለመቆጣጠር በሚፋለሙበት በዚህች ቁልፍ ከተማ ወደ ግጭት እንዳይገቡ በማሰብ የፌደራል ሠራዊቱ እና የሠራዊቱ አጋር ኃይሎች ከተማዋን ለቀው እንዲወጡ የ72 ሰዓት ቀነ ገደብ ያቀስመጡት ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
