” የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ለተፈጠሩት ችግሮች መፍትሔ በመስጠት ሐዋርያዊ አደራውን እንዲወጣ በልጅነት መንፈስ ዝቅ ብለን እንማፀናለን! ” የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት

Date:

የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ግንቦት 6 ቀን 2017 ዓ.ም በተደረገ ስብሰባ የዘንድሮ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ በርካታ ሥር ነቀል ለውጦችን ማምጣት የሚችል ፤ ለነገይቱ የቤተክርስቲያን ተረካቢ ወጣቶች መሰረት የጣለ እንዲሆን ያለመ ምክረ ሐሳብ ተወያይቶ ማቅረቡን አስታውቋል።

ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ቀርበው መፍትሔ እንዲሰጥባቸው ከቀረቡት ውስጥ ፦ የቤተክርስቲያንን ሲኖዶሳዊ ልዕልና እና አንድነትን ማስጠበቅ ፣ የቤተክርስቲያንን አስተዳደራዊ ችግሮችን በመለየት መፍታት ፣ የሥነ ምግባር ግድፈት እና የቀኖና ጥሰት መበራከት ፣ በሀገራዊና ዓለም አቀፍ ጉዳይ ላይ የሚኖሩ ተሳትፎዎች ዋና ዋና ጉዳዮች ስለመሆናቸው በመልእክቱ ተላልፏል።

ሐሰተኛ የሆኑ የኑፋቄ ትምህርቶች ፣ በሰላም እጦት የሚገኙ አህጉረ ስብከቶች ፣ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ሚና ፣የሀብት ብክነት ፣ ዘመኑን የዋጀ የአሠራር መንገድ መዘርጋት ፣ መንፈሳዊ አገልግሎት ላይ የሚስተዋሉ እና አፈንግጠው የወጡ ሥርዓቶች ፣ በከተማ ልማት መስፋፋት የምእመናን ከአምልኮ ሥፍራ መራቅ ፣ ሀገራዊ የችግር አፈታት መንገዶች ላይ ምልዓተ ጉባኤውም በስፋት እንዲወያይ አንድነቱ በዝርዝር ካስቀመጣቸው ሐሳቦች መሐል ይገኙበታል።

እነዚህን እና ሌሎች የውይይት ሐሳቦችን በዝርዝር በማቅረብ ” የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መፍትሔ በመስጠት ሐዋርያዊ አደራውን እንዲወጣ በልጅነት መንፈስ ዝቅ ብለን እንማፀናለን! ” በማለት አንድነቱ መልእክቱን አጋርቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...