ቱርክ በጦርነት ለሚፈናቀሉ ሱዳናውያን ሴቶች የማገገሚያና የትምህርት ማዕከል መክፈቷ ተገለጸ

Date:

የማገገሚያ ተቋሙ በጦርነቱ  ለተጎዱ ሴቶች፣ ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸውና የስነልቦና ቀውስ ለገጠማቸው ሴቶች አገልግሎት የሚሰጥ ነዉ ተብሏል፡፡

የቱርክ የእርዳታ ድርጅት ኤጀንሲ ቲካ ፤ ሱዳናውያኑን ለማገዝ በፖርት ሱዳን ላይ ደህንነቱ የተጠበቀ ማዕከል ከፍቻለሁ ብሏል፡፡

ተቋሙ የተከፈተው በተለይም በጦርነቱ ምክንያት ከካርቱም ገዚራና ሴናር ከተባሉ ከተሞች የተፈናቀሉ ሴቶች የሚያርፉበት እንደሆነ ተገልጿል፡፡

ሴቶቹ በጦርነቱ ምክንያት የተለያዩ ችግሮች የገጠማቸው እንደሆኑ የተገለጸ ሲሆን፤ ከነዚህ ችግሮችም እንዲወጡ የተለያዩ ስልጠናዎችና ትምህርቶች እንዲሁም ድጋፎች እንደሚሰጣቸዉ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

ሶስት አመት በሞላው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት  በሚሊዮኖች ሲፈናቀሉ 20ሺህ የሚጠጉ ሱዳናውያን ህይወታቸውን ማጣታቸዉን የዘገበው አናዶሉ ነው፡፡

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

ንባብ ለሕይወት ባዛር እየተካሄደ ነው !!!

በንባብ ለሕይወት ፕሮጀክትና በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አዘጋጅነት የሚካሄደው...

በኢራን የኤነርጂ መሠረተ ልማቶች ላይ ያነጣጠረ አዲስ መጠነ ሰፊ ጥቃት መታቀዱ ተሰማ

የአሜሪካ ጦር በዚህ ሳምንት መጨረሻ በኢራን ላይ አዲስ ጥቃት...

የብሔር ፌደራሊዝምን ለማስቀጠል “የቆረጡ” ተመካካሪዎች

በሀገራዊ የምክክር ጉባኤ 14ኛ ቀን ውሎ “ስልታዊ” ቡድኖች የአጀንዳ...

“የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው” ፓትርያርኩ

የሩሲያ ክርስቲያኖች ከኢራን ሙስሊም ማህበረሰብ ጋር መልካም ግንኙነት አላቸው...