የቅዱስ ሲኖዶስ አረጋውያን ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ለዕድሜ ልክ አገልግቶታቸው  ዕውቅና ሊሰጥ ነው

Date:

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚሁ ዕለት የተመለከተው የተለየ አጀንዳ፤ ለረጅም ዘመን ቤተክርስቲያንን ያገለገሉ ብፁዓን አባቶችን የተመለከተ ነው፡፡ በዚህም ላይ ውይይት አድርጎ የሚከተለውን ውሳኔ አሳልፏ፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ አማካኝነት በኤጲስ ቆጶስነት ተሹመውና በየአህጉረ ሰብከቱ ተመድበው ለረጅም ዘመን ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን መዋቅርና ትውፊት ጠብቀው፣ የሚያስፈልገውን መሥዋዕትነት ሁሉ ከፍለው፣ ለቤተ ክርስቲያን ልዕልና’ ለሐዋርያዊ ተልዕኮ መስፋፋትና ለእናት ቤተክርስቲያን ተቋማዊ እድገት የዕድሜ ልክ አገልግሎት የሰጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፡-

ብፁዕ አቡነ ታዴዎስ የካሪቢያንና የላቲን አሜሪካ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ የሰሜን ወሎ ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ዮናስ የአፋር ሀገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ 

ብፁዕ አቡነ ስምዖን የመንበረ ፓትርያርክ  ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የበላይ ኃላፊ ሊቀ ጳጳስ ሌሎችም አረጋውያን ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በምልዓተ ጉባኤው ዕውቅና እንዲሰጣቸው ሆኖ የሚሰጠው ዕውቅና የሚታይና የሚታወስ እንዲሆን፤ አፈጻጸሙም ደግሞ በቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤትና በጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል ሳይዘገይ እንዲፈጸም በማለት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

©EOTC TV

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...