የቤላሩስ ፕሬዚዳንት የኢትዮጵያን ባህር በር ፍላጎት ደገፉ

Date:

የቤላሩስ ፕሬዝዳንት አሌክሳንደር ሉካሼንኮ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነትን ለማጠናከር ሀገራቸው ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቁ። በተለያዩ ዘርፎች ትብብርን ለማስፋት ጠንካራ “ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት” እንዳላቸውም ገልጸዋል።

“ኢትዮጵያ ለእኛ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙት በጣም አስፈላጊ አገሮች መካከል አንዷ ናት” ያሉት ፕሬዚዳንቱ፤ ቤላሩስ የቴክኖሎጂ፣ የግብርና እና የምህንድስና ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን ተናግረዋል።

ፕሬዚዳንቱ ቤላሩስ ለኢትዮጵያ የግብር ማሽነሪዎችን ድጋፍ ለማድረግ፣ ቴክኖሎጂን ለማስተላለፍ እና የኢትዮጵያ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን ዝግጁ መሆኗንም ገልጸዋል።

በጥቅምት ወር የቤላሩሱ መሪ ኢትዮጵያ የባህር መዳረሻ ለማግኘት ያላትን ፍላጎት በብርቱ ደግፈዋል። የሀገሪቱ ሚዲያ እንደዘገበው፤ ሉካሼንኮ የኢትዮጵያን የባህር በር የማግኘት ፍላጎትን የሚቃወሙ “ፍጹም ሞኞች” ናቸው ብለዋል።

አክለውም “በጦርነት ወይም በድርድር ኢትዮጵያ ወደ ባህር በር ትደርሳለች። በእርግጥም በሰላማዊ መንገድ ቢሆን የተሻለ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

አክሊሉ ወንድሞቹ ለንባብ በቃ

በፀሐፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ የልጅነት ታሪክ ላይ ያተኮረ ለታዳጊዎች...

የኢራን ተፈጥሮአዊ ምሽጎች እና ስትራቴጂካዊ ጥበብ

​ግዮን መጽሔት :- በመካከለኛው ምስራቅ የጂኦ-ፖለቲካ ትኩሳት...

ለአድዋ ድል መታሰቢያ በአሜሪካ ቀን ተሰየመ

በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት...

ኢሎን መስክ የዓለማችን የመጀመሪያው ትሪሊዮነር ሆነ

ኢሎን መስክ የሀብት መጠኑ 1 ትሪሊዮን ዶላር ያለፈ የመጀመሪያው...