የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ 35ኛ ዓመት በዓለ እረፍታቸው ታስቦና ተከብሮ ዋለ

Date:

የብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ 35ኛ ዓመት የእረፍታቸው መታሰቢያ በዓል በዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሣዊ ኮሌጅ ፡ ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ በተገኙበት ተከብሮና ታስቦ ውሏል።

መርሓ ግብሩ በብፁዕነታቸው ቡራኬና ጸሎት ተከፍቶ በገዳሙ የሰንበት ት/ቤት ዘማርያን እንዲሁም በማኅበረ ጎርጎርዮስ ዘአንባ ደብረ መዊዕ ሕፃናትና የወጣቶች ጥምረት ዝማሬ ቀርቧል።

በመቀጠል በብፁዕነታቸው መልካም ፈቃድ በመጋቤ ብሉይ ወሐዲስ ቆሞስ አባ አትናቴዎስ ወልደ ጎርጎርዮስ ትምህርተ ወንጌል ተሰጥቷል። በተያያዘም በማኅበረ ጎርጎርዮስ ዘአንባ የተዘጋጀ መንፈሣዊ ዶክመንተሪ ፊልም ቀርቧል።

በመጨረሻም ብፁዕ አባታችን አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መልእክት አስተላልፈው በቃለ ምዕዳንና ጸሎት መርሓግብሩ ተጠናቋል።

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ ሐምሌ 22 ቀን 1982 ዓ/ም ከጠዋቱ 1÷30 በመቂ ደብረ አሚን ቅዱስ ጊዮርጊስና በቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለሚገኙ ምእመናን ትምህርተ ወንጌል ለመስጠት ሲፋጠኑ በድንገተኛ የመኪና አደጋ በተወለዱ በ50 ዓመታቸው ማረፋቸው የሚታወስ ነው ።

Hameretewahedomedia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኢራን ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን በድጋሚ መዝጋቱን የአገሪቱ መገናኛ ብዙኃን ዘገቡ

የኢራን መገናኛ ብዙኃን የአገሪቱ ጦር የሆርሙዝ ወሽመጥን ዳግም መቆጣጠር...

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት ክብረ በዓል

ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አስመልክቶ...

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለ20 አትሌቶች  የማስጠንቀቂያ አውጥቷል

በውድድሩ ላይ ያልተገኛችሁ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ይመለከታል የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ዓለምአቀፍ...

የአሜሪካ እና የኢራን ድርድር፤ ለወረራ የታለመ ማደናገሪያ? ሩሲያ ማስጠንቀቂያ ሰጠች!

በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የሚደረገው ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ውጥረትን ለመቀነስ...