የሞታቸዉን ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው

Date:

ህንዳዊ ዜግነት ያላቸው ግለሰብ አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ መገኘቱን በኢትዮጵያ የህንድ ኢንባሲ አስታወቀ።

ህንዳዊ ዜግነት ያለው እና በአዳማ አከባቢ ቢሮውን ባደረገው በካልፓታሩ ፕሮጀክት ኢንተርናሽናል ሊሚትድ በተሰኘ ተቋም (KPIL) ሲሰራ የነበረ ግለሰብ በአዳማ አከባቢ ሞቶ መገኘቱን በኢትዮጵያ የሚገኘው የህንድ ኤምባሲ አስታውቋል።

ኤምባሲው ባወጣው አጭር መግለጫ ናቭ ሱቫሪዮ የተሰኙትና በአዳማ-አዋሽ ፈጣን መንገድ ፕሮጀክት ላይ የተቋሙ ምክትል ሥራ አስኪያጅ ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩት ግለሰብ፥ ” አስክሬናቸው በአዳማ ፖሊስ የተገኘ ሲሆን የሞቱን ትክክለኛ መንስኤ ለማጣራት ምርመራ እየተካሄደ ነው ” ሲል አስታውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ስለ ጉዳዩ ለማጣራት ወደ ሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች ተደጋጋሚ የስልክ ጥሪ ቢያደርግም ለጊዜው ምላሽ ማግኘት አልቻለም።

@tikvahethiopia

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

“ሕገ መንግሥቱ መገንጠልን ይፈቅዳል ፤ ሕዝቡ ደግሞ ኢትዮጵያ እንድትቀጥል ዋጋ ይከፍላል”

አቶ ፍሬሕይወት ሳሙኤል(የ‹‹ሕገ መንግሥታዊ ተቃርኖዎች›› መጽሐፍ ደራሲ) ግዮን መጽሔት :-...

ባለሙያ ባልሆኑ ግለሰቦች የሚሰራጭ የተዛባ መረጃ በታካሚዎች ላይ ጉዳት እያደረሰ ነዉ

የሳይካትሪስት የሙያ ፈቃድና ሥልጠና የሌላቸው ግለሰቦች በተለያዩ መገናኛ...

የአውሮፓ ህብረት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የ1.2 ቢሊዮን ዩሮ ስምምነት ሊፈራረሙ ነው

በአውሮፓ ህብረት እና በኢትዮጵያ መካከል በሚካሄደው የንግድ ፎረም መክፈቻ...

የአዳዲስ እና የሁለተኛ ዙር መራጮች አቅምና ሚና

ግዮን መጽሔት :- በ7ኛው አገራዊ ምርጫ ላይ የአዳዲስ (ለመጀመሪያ...