የአሜሪካው ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ከቴህራን ጋር ለመነጋገር ወደ ስዊዘርላንድ የሚደርጉትን ጉዞ አዘገዩ።
ቫንስ ጦርነቱን ለማቆም የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸውን ተከትሎ፥ ከኢራን ጋር አዲስ የውይይት መድረክ ለመምራት ወደ ስዊዘርላንድ ሊያደርጉት የነበረውን ጉዞ አዘግይተዋል ተብሏል።
ዋይት ሀውስ እንዳስታወቀው፥ መዘግየቱ በተወሳሰቡ የሎጂስቲክስ ምክንያቶች የተከሰተ ቢሆንም፣ የአሜሪካ ልዑካን ቡድን በማንኛውም ጊዜ ጉዞውን ለማድረግ ዝግጁ ነው።
የውይይቱ ዓላማ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር የፈረሙትን የቀጠናው ጦርነት ማብቂያ እና የኢራንን የኒውክሌር መርሃ ግብር የሚገድበው ስምምነት ዝርዝር ሁኔታዎችን ለማካተት የታቀደ ቴክኒካዊ ውይይት ነው።
የጉዞው ጊዜ እርግጠኛ ባይሆንም፣ አሜሪካ በስምምነቱ መሰረት በኢራን ወደቦች ላይ የነበራትን የባህር ላይ አግዳ ማንሳቷን እና በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ በርሜል ነዳጅ የጫኑ መርከቦች ወደ ሆርሙዝ ሰርጥ መዘዋወር መጀመራቸውን አስታውቃለች።
በሌላ በኩል ኢራን በደቡባዊ ሊባኖስ እየተካሄደ ባለው የእስራኤል ጥቃት፥ ልዑካን ቡድኗን ወደ ስዊዘርላንድ ለመላክ መስተጓጎሏ ተሰምቷል።
ዘገባው የቢቢሲና አሶሼትድ ፕረስ ነው።
