የነዳጅ እጥረት አሽከርካሪዎችን ለከፋ እንግልት እየዳረገ ነው

Date:

በአዲስ አበባ እና በልዩ ልዩ የክልል ከተሞች የሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት ከቀን ወደ ቀን እየተባባሰ መምጣቱ በአሽከርካሪዎችና በነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጫና እያሳደረ ይገኛል።

በቅርቡ የተደረገውን የዋጋ ጭማሪ ተከትሎ የተከሰተው የአቅርቦት ማነስ፤ በተለይም በመቀሌ፣ በጅማ፣ በአምቦ እና በባሕር ዳር ከተሞች አሽከርካሪዎችን ለረጅም ሰዓታት የሰልፍ እንግልት ዳርጓቸዋል።

በመቀሌ አንድ የ20 ሊትር ነዳጅ በህገ-ወጥ መንገድ እስከ 8,000 ብር እየተሸጠ መሆኑን የሚገልጹት ተጎጂዎች፣ ሰዓታትን በሰልፍ ቢያሳልፉም ነዳጅ የማግኘት ዕድላቸው አነስተኛ መሆኑን በምሬት ይናገራሉ።

ሁኔታው የሕዝብ ትራንስፖርት እንቅስቃሴን ከማስተጓጎሉም በላይ፣ አሽከርካሪዎች የሥራ ሰዓታቸውን በማደያዎች ሰልፍ ላይ እንዲያባክኑ አስገድዷቸዋል።

ችግሩ በዚህ ከቀጠለ የትራንስፖርት ዘርፉ ክፉኛ ሊጎዳ ይችላል የሚል ስጋት የነገሰ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አካላት ለአቅርቦት መቆራረጡ አስቸኳይ መፍትሔ እንዲፈልጉ ተጠይቋል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

እንግሊዝ ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች ማህበራዊ ሚዲያ እንዳይጠቀሙ አገደች

የእንግሊዝ መንግሥት ዕድሜያቸው ከ16 ዓመት በታች የሆኑ ሕፃናትና ታዳጊዎች...

አሜሪካ 300 ሚሊዮን ዶላር ለኢራን ልትሰጥ ነው መባሉን ትራምፕ አስተባበሉ

አሜሪካ እና ኢራን ከስምምነት ከደረሱ በኋላ አሜሪካ እና አጋሮቿ...

ደህና ሁን! ሰሜ…ስሜ!

“ከልጅነታችን ጀምሮ ጥበብ አገናኝታን ፣ በግሽ አባይ የባህል ቡድን...

✌️ጀግናን ማክበርና መሸለም ጀግንነት ነው

✌️ከዕድሜው የገዘፈው የታሪኩ ጁዋር ጀግናውን ሙሉጌታ ከበደን የመዘከር የጀግንነት...