የአሜሪካ የኒውክሌር ኤጀንሲ በምሥጢራዊ የመረጃ ምንተፋ ተጠቃ

Date:

የአሜሪካ የኒውክሌር ግምጃ ቤት በኃላፊነት የሚመራው ብሔራዊ የኒውክሌር ደሕንነት አስተዳደር፤ የማይክሮሶፍት ሼር ፖይንት የሰነድ አስተዳደር ሶፍትዌር ብልሽትን በመጠቀም ተጠልፏል፡፡ 

🔍 የአሜሪካ ብሔራዊ የኒውክሌር ደሕንነት አስተዳደር፣ የኒውክሌር ጦር መሣሪያዎችን የመገንባት፣ የማፍረስ እና የመጠበቅ ኃላፊነት የተሰጠው በከፊል ራሱን የሚያስተዳድር የኢነርጂ መምሪያ ቅርንጫፍ ነው።

🔍 አስተዳደሩ የኒውክሌር ሰርጓጅ መርከብ ሬአክተሮችን ማስተዳደር፣ ለጨረር አደጋዎች ምላሽ መስጠት እና ሽብርተኝነትን መመከት ሥራው ነው፡፡ ሌሎች የመምሪያው ክፍሎችም ተጠቅተዋል፡፡

ይህኛው ምንተፋ ወሳኝ የአሜሪካ ብሔራዊ ዘርፎች ላይ ያነጣጠረው ተከታታይ ጥቃት አካል ነው፡፡

➡️ በመጋቢት ወር ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ እና የመከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴዝን ጨምሮ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለሥልጣናት የሲግናል መተግበሪያ የቡድን ውይይት አፈትልኳል፡፡ እነዚህ መልዕክቶች ከኦፕሬሽን ጥቃት መረጃዎች እስከ የሲአይኤ ሰላይ ማንነት ድረስ ሁሉንም ነገር የያዙ ነበሩ፡፡

ስፑትኒክ ኢትዮጵያ

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የኮሪያ ዘማቾች ያስመዘገቡት አኩሪ ታሪክ በዓለም ሲታወስ ይኖራል

75ኛ ዓመት የኮሪያ ዘማቾች መታሰቢያ በዓል አዲስ አበባ በሚገኘው...

አሜሪካ በጣለችው የባህር ላይ እገዳ ሳቢያ ኢራን 4.8 ቢሊዮን ዶላር አጣች

በአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትዕዛዝ በኦማን ባህረ ሰላጤ ላይ...

ኢሕአፓ ሊያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ ማራዘሙን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢሕአፓ) ሚያዚያ 30 ቀን 2018...

እሁድ መንገዶች ለተሽከርካሪዎች ዝግ ይደረጋሉ

መነሻውንና መድረሻውን መስቀል አደባባይ የሚያደረገው ዓለም አቀፉ የዛይድ የበጎ...