የአንድ ሰው ህይወት አልፏል ፤ 3 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ” – ፖሊስ

Date:



ከባድ የአካል ጉዳት ከደረሰባቸው መካከል የ7ኛ እና የ5ኛ ክፍል ሴት
ተማሪዎች ይገኙበታል። “

በአዲስ አበባ የተባበሩት አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ በአንድ ሰው ላይ የሞትና በሦስት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ አስታወቀ፡፡

መጋቢት 23 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1፡00 ሠዓት በለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 13 ልዩ ቦታው የተባበሩት አደባባይ አካባቢ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3A-41968 አ/አ የሆነ አልያንስ የህዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ ከአቤም ወደ የተባበሩት አቅጣጫ ቁልቁለቱን በመጓዝ ላይ ሳለ ከአያት ወደ ሲ.ኤም.ሲ አቅጣጫ እየተጓዙ ከነበሩ የሠሌዳ ቁጥሩ ኮድ 3-35090 አ/አ እና የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3B-57071 አ/አ ቪትዝ የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በመግጨት የተባበሩት አደባባዩ ላይ በመውጣት ሊገለበጥ ችሏል፡፡

በአደጋውም የፒካፕ መኪናው አሽከርካሪ ህይወት ወዲያውኑ ሲያልፍ በውስጡ ተሳፍረው የነበሩ ሁለት የ7ኛ እና የ5ኛ ክፍል ሴት
ተማሪዎች እንዲሁም የቪትስ መኪናው አሽከርካሪ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

” አሽከርካሪዎች ሁሌም ቢሆን የመንገዱን ሁኔታና አቀማመጥ በሚገባ በማጤን ተሽከርካሪያቸውን መቆጣጠር በሚያስችላቸው ሁኔታ ሊያሽከረክሩ ” ይገባል ያለው ፖሊስ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ለተጎጂዎችም ብርታትን ተመኝቷል።

ያጋሩ!

መጽሔቶች

በብዛት የተነበቡ

ተጨማሪ ጽሑፎች
ተመሳሳይ

የአርቲስት ጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ

ለኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ ዕድገት ወደር የሌለው አስተዋጽኦ ላበረከተውና የሙዚቃው...

ሕወሓት ድብረጺዮንን የክልሉ ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ

የክልሉ ፕሬዚዳንት ተደርገው የተመረጡት  ድብርጺዮን ገ/ ሚካዔል (ዶ/ር)  ቃለ...

” ኢራን ከምድረ ገጽ ትጠፋለች ” – ትራምፕ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ጋር ቃለ...

የአርበኞች ድል መታሰቢያ እና የዛሬው ትውልድ ለሕብረት ያለው አቋም

የጥንት ኢትዮጵያዊያንአርበኞች ድል 85 ኛው ዓመት መታሰቢያ ሚያዚያ...