የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ በሊዝ የሚተዳደሩ 2,969 ቦታዎች ወደሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ የአገልግሎት ለውጥ ጥያቄዎችን ተቀብሎ ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።
በእስካሁኑ ተፈቅዶላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉ ባለይዞታዎች 2,969 ሲሆኑ 2,581 (86%) የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን ቅድመ ክፍያ ከፍለው በማጠናቀቅ ወደ ሕጋዊ ሥርዓት እንዲገቡ ወይም የንግድ ሥራቸውን እንዲቀጥሉ ተደርጓል ነው ያለው።
በበጀት ዓመቱ ከዚህ የአገልግሎት ለውጥ 2.4 ቢሊዮን ብር ገቢ ይሰባሰባል ተብሎ እንደሚጠበቅ የአዲስ አበባ ከተማ መሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ገልጿል።
ሳይፈቀድላቸው የአገልግሎት ለውጥ ያደረጉና ለውጥ የተፈቀደላቸው የሊዝ ባለይዞታዎች የሚጠበቅባቸውን የሊዝ ቅድመ-ክፍያ እስከ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም ድረስ ከፍለው ማጠናቀቅ እንደሚጠበቅባቸውም ቢሮው አሳስቧል።
