አዲስ አበባ ፒያሳ አካባቢ የሚገኘዉ እድሜ ጠገቡ አንበሳ ፋርማሲ መፍረሱን በስፍራው ተገኝቶ አረጋግጣል። እየፈረሰ ያለው አንበሳ ፋርማሲ ከተመሰረተ 80ኛ ዓመቱን የያዘና ጥንታዊ እንደሆነ ይታወቃል፡፡
በጀርመናዉያን ሁለተኛ እና በሦስተኛ ትዉልድ እየተንቀሳቀሰ የነበረው አንጋፋዉ አንበሳ መድሐኒት ቤት የመድሐኒት ሽያጭና ቅመማ ብቻ ሳይሆን የሕክምና ቁሳቁስ አስመጭና አገር ውስጥ አከፋፋይም ነበር ።
ከዓመታት በፊት አንበሳ ፋርማሲ ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚገኘዉ የጀርመን ኤምባሲ የአንበሳ መድሐኒት ቤትን ድጋፍ መስጠትን ይመለከታል በሚል ለአዲስ አበባ ከተማ የወቅቱ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ በፃፈዉ ደብዳቤ አዲስ አበባን ብሎም ኢትዮጵያን የጀርመን የመዋለ ንዋይ ፍሰት መዳረሻ ለማድረግ እንደሚያበረታታ አንድ ኤምባሲ፤ ጉዳዩ ሕጋዊ መንገድን መከተል አለበት ብለን እናምናለን። ምክንያቱም በእድሜ ጠገቡ የአንበሳ መድሐኒት ቤት ላይ አስተዳደሩ ይወስዳል የተባለዉ ርምጃ ሌሎች የጀርመን ባለ ኃብቶችን ሊያሸሽ ይችላል ሲል ደብዳቤ ማግባቱ በወቅቱ ተዘግቧል።
አንበሳ ፋርማሲ የሚገኝበት አነስተኛ ህንጻ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሲሆን ከአመታት በፊት ከአካባቢ ልማት ጋር በተያያዘ ፋርማሲው ይፈርሳል ተብሎ የሚናፈሰው መረጃ ፍጹም ከእውነታው የራቀና መሰረተ ቢስ መረጃ ነው ሲል ኮርፖሬሽኑ ማስተባበሉ የሚታወስ ነው።
ከቅዳሜ ገበያ
