Home ዋናው ጤና የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ምንድን ነው?

የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ምንድን ነው?

የአጥንት መሳሳት (Osteoporosis) ምንድን ነው?

“Osteoporosis” የምንለው የሰውነታችን የአጥንት መሳሳት ችግር ሲሆን የአጥንት የሚነራል ክምችት (Bone mineral density) በእጅጉ እንዲቀንስ የሚያደርግ ችግር ነው። በአለም ላይ በየአመቱ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በዚህ ችግር ተጠቂ ነው። አጥንቶቻችን ያለማቋረጥ ሊሰባበሩ የሚችሉ ከዛም በምትካ አካል ነው። ነገር ግን አዲስ አጥንት መተካት ሳይችል ሲቀር የአጥንት መሳሳት ሊያመጣ ይችላል።

ማንን ያጠቃል፡-

የአጥንት መሳሳት ሴቶችም ወንዶችም ላይ ሊከሰት የሚችል በተለይም እድሜያቸው ገፋ ያሉ ሴቶች ላይ እና ከማረጥ በዃላ (post menopause) ፣ እድሜ እየገፋ ሲሄድ የEstrogen hormone እየቀነሰ ስለሚሄድ ፣ ወንዶች ላይ ደግሞ የtestesretone hormone ማነስ መንስኤ ሊሆኑ ይችላሉ ምክንያቱ ደግሞ እነዚህ hormones ለአጥንት መጠንከር አስፈላጊ ስለሆኑ ነው።

ለአጥንት መሳሳት የሚያጋልጡን ተጨማሪ ነገሮች፡-

• የተመጣጠነ ምግብ እጥረት (Malnutrition)

•መድሀኒቶች ለምሳሌ Corticosteroid የምንላቸው ለቀላሉም ለከባዱም ህመም በተደጋጋሚ የምንወስዳቸው  ማስታገሻዎች ፣ ለአስም የሚወሰዱ, በተጨማሪ • Anticonvulsant የምንላቸው የሚጥል በሽታ መድሀኒቶች

• ሲጋራ ማጨስ ፣ አልኮል መጠጥ

• የኩላሊት ፣ የጉበት ችግር ፣ የአንጀት መቆጣት ችግር

ምልክቶቹ

• በአብዛኛው ጊዜ የአጥንት መሳሳት ስበራት እስኪኖር ድረስ ምልክት ላያሳይ ይችላል።

• ምልክት የሚያሳይ ከሆነ አጥንት አካባቢ የህም ስሜት፣ የቁመት መቀነስ(height loss)

የሚያመጣውስ ችግር፡-

• በመውደቅ ወይም በግጭት አንዳንዴ ጎንበስ ስንል እንኳን የአጥንት መሰበር በተለይም የጀርባ አከርካሪት እና የዳሌ አጥንት ስብራት በቀላሉ መሰበር (Hip fracture) እሰከ የእለት ከእለት አንቅስቃሴ ማገድ ድረስ፣ሊያደርስ ይችላል። ይህ ሲሆን ደግሞ የሰውነት ክብደት መጨመር ከዛም ከውፍረት መጨመር ጋር ተያይዞ ለስኳር ፣ ለልብ በሽታ ተጋላጭነት ይጨምራል።

• የአከርካሪ እና የዳሌ አጥንት ስብራት እሰከ ሞትም ሊያደርስ ይችላል።

እንዴት መከላከል እንችላለን፡-

• በቂ የሆነ የፀሀይ ብርሀን ማግኘት Vitamin D የምናገኝበት ስለሆነ እና Vitamin D ደግሞ ለአጥንት ጥንካሬ በጣም ወሳኝ እና ዋነኛው ነገር ነው

• የተመጣጠነ በካልሽየም የበለፀጉ ምግቦችን መመገብ ለምሳሌ ወተት እና የወተት ተዋፅኦ ፣ የአሳ ምርቶች እንዲሁም በzinc ፣ magnesium ፣ የበለፀጉ ምግቦች ፣ የብርቱካን ጭማቂ

• በቂ የአካል በቃት እንቅስቃሴ ማድረግ

• ተመጣጣኝ የሰውነት ክብደት እንዲኖረን ማድረግ

• ቡና እና ጨው አለማብዛት ምክንያቱም ካልሽየም በብዛት በሽንት እንዲወጣ ስለሚያደርጉ

የአጥንት መሳሳት  እንዴት ማረጋጋጥ እንችላለን፡-

• የአጥንት ሚንራል ክምችት በcentral dual-energy x-ray absorbitometry (DXA) ታይቶ መረጋገጥ ይችላል።

ሕክምናው፡-

• አጥንት እንዲደራጅ እና የስብራት ተጋላጭነት አንዲቀንስ የሚያደርጉ መድሀኒቶች መስጠት የአጥንትን የሚነራል ክምችት ሙሉ በሙሉ መመለስ ባይቻልም በተወሰነ መለኩ መመለስ ይችላል።

• ያረጡ ሴቶች ላይ Estrogen የመተካት ህክምና።

ሕፃናት የወይራ ዘይት መቼ መጀመር አለባቸው?

ከ6 ወር ጀምሮ ምግባቸው ላይ ጠብ እያደረግን መመገብ እንችላለን፡፡ ተጨማሪ ምግብን በተመለከተ ኤክስትራ ቨርጅን የወይራ ዘይት የተሻለ እና ተስማሚ ነው። የወይራ ዘይት ስብጥር ለሚያድግ አካል በጣም አስፈላጊ የሆኑት “ጠቃሚ” ኮሌስትሮል እና ያልተሟሉ የሰባ አሲዶች አሉት(fatty acid) ቅንብሩ በተጨማሪ በጡት ወተት ውስጥ ከሚገኙ ቅባቶች ጋር ተመሳሳይነት ያላቸውን ቅባቶችን ያጠቃልላል፡፡ የወይራ ዘይት ከሌሎቹ የአትክልት ዘይቶች ሁሉ በተሻለ የህጻናት ሰውነት ላይ  በዳይፐር አማካኝነት የሚፈጠርን ሽፍታ ለማጥፋት፣ እንዲሁም ህፃናት ላይ የሚወጣን ብጉር ለማጥፋት ይጠቅማል፡፡

በሕፃናት ላይ የሚከሰት የአፍ ውስጥ ፈንገስ ምንድን ነው?

የሕፃናት የአፍ ውስጥ ፈንገስ የሚከሰተው ፈንገሱ በአፍ ውስጥ አድጎ በሚፈጥረው ኢንፌክሽን ምክንያት ነው፡፡ ይህ ኢንፌክሽን ብዙን ጊዜ ሕፃናት ለከፋ ጉዳት የማይጥል ቢዠኾንም አልፎ አልፎ ግን ከባድ የጤና ችግር የሚኾንበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ በተለይ የተፈጥሮ የበሽታ የመከላከል አቅማቸው በተለያዩ ምክንያቶች የተዳከመ ከሆነ ኢንፌክሽኑ ወደ ተለያየ የሰውነት ክፍላቸው በመዛመት ውስብስብ የጤና ችግር የማምጣት እምቅ  አለው፡፡ በተመሳሳም ከሰው ወደ ሰው በቀላሉ ይተላለፋል፡፡

የአፍ ውስጥ ፈንገስ መንስኤዎች በልጆች ላይ፡-

ካንዲያሲስ ፈንገስ አልቢካንስ ሲ በተባለ ፉንገስ አማከኝነት ሊከሰት ይችላሉ፡፡ እናቶች ብዙን ጊዜ ወተት እንዳይፈስ በማለት ጡታቸውን የሚሸፍኑባቸው ነገሮች አማካኝነት ባክቴሪያዎች ሊፈጠሩ ይችላሉ፡፡ በእርግዝና ጊዜ እናት ማህፀን ኢንፌክሽን ተጋልጣ ሳትታከም ከቀረች በምቶልድበት ሰአት ከስዎ ወደ ልጁ በመተላለፍ ልጁ ላይ የአፍ ውስጥ ፈንገስ ሊያስከትልበት ይችላል፡፡ እናት በምታጠባበት ወቅት ህመም እና ከጡቷ ጫፍ የሚወጣ ፈሳሽ ካለ ከወተት ወጪ እነዚህ ካሉ ኢንፊክስን ተፈጥሮ ሊሆን ስለሚችል በሚያጠቡበት ወቅት ወደ ህፃኑ ስለሚተላለፍ የአፍ ውስጥ ፈንገስ ሊያስከትልበት ይችላል ስለዚህ ህክምና ማድረግ ይኖረባቸዋል::

የአፍ ውስጥ ፈንገስ ምልክቶች፡-

ነጭ ወይም ቢጫ ቀለም ያላቸው ያበጡ ነገሮች በትንሽ ቦታ ላይ ውስጠኛው ጉንጭ ክፍል፣ በምላስ፣በቶንሲሎች፣ በድድ ወይም በከንፈር ላይ ይወጣሉ፡፡ እብጠቱ በሚፋቅበት ጊዜ አነስተኛ ደም ይወጣዋል፤ በአፍ ውስጥ ቁስል ወይም የማቃጠል ስሜት ይፈጠራል፤ የጥጥ ስሜት አፍ ውስጥ መሰማት፤ በአፍ ጥግ ላይ መድረቅና የቆዳ መሰንጠቅ ሊያጋጥም ይችላል፤ ለመዋጥ መቸገር የአፍ መጥፎ ጠረን ሊፈጠር ይችላል፤ ምግብ የማጣጣም አቅም መቀነስ ወይም ጣእም ማጣት አንዳንዴም የምግብ መውረጃ ትቦ (ኦሶፋገስ) በዚህ ኢንፌክሽን ሊጠቃ ይችላል፡፡

በቤት ውስጥ ማድረግ የምንችለው ምንድን ነው፡-

የሕፃናቱን እድሜ ባማከለ መልኩ ለልጆች እርጎን መስጠት እንችላለን፡፡ እረጎ ላክቶስ በሲላይ የተባለ እጥረ ነገርን ስለያዘ ፈንፈፉን ለመቀነስ ይረዳናል፤ ለብ ባለ ውሃ ላይ ጨው በመጨመር አካባቢውን መጥረግ፡፡

ሕክምናው፡- የአፍ ውስጥ የሕፃናት ፈንገስ ለማከም የጤና ባለሙያዎ የሚታዘዙ መድኃኒቶችን ይኖራሉ፡፡ እነዚህ መድኃኒቶች ፀረ- ተዋህሲያን መድኃኒቶች ሲሆኑ ከፍተኛ ጥንቃቄ የሚጠይቁና በትክክል ሊወሰዱ የሚገባቸው ናቸው፡፡